
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 17/2015 NBC Ethiopia- ምክር ቤቱ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 19/2015 ዓ.ም በሚያካሂደው መደበኛ ጉባኤው የ2015 በጀት ዓመት የአስፈጻሚ አካላት ሪፖርት፣ የም/ቤት ጽ/ቤት ሪፖርት፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት ዓመታዊ ሪፖርት አድምጦ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
በተጨማሪም የ2016 በጀት ዓመት የክልሉን በጀት ረቂቅ አዋጅና የተለያዩ ሹመቶችን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ወይዘሮ ዓለምነሽ ይባስ በጉባኤው ማስጀመሪያ ላይ፣ በክልሉ አሁን የታዬየውን ሠላም በመጠቀም በህዝቡ የሚነሱ የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ የበለጠ መሥራት ይጠበቅብናል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia










