
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 17/2015 NBC Ethiopia- አፍሪካ የዓለምን እጣ ፋንታ በሚወስኑ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ተገቢውን ቦታ ለማግኘት እያደረገች ያለችውን ጥረት እንደግፋለን” ሲሉ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገለጸዋል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዚህ ሳምንት የሚካሄደውን የሩሲያ አፍሪካን ጉበኤ ምክንያት በማድረግ በላኩት ጽሁፍ፤ አፍሪካ የዓለምን እጣ ፋንታ በሚወስኑ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ተገቢውን ቦታ ለማግኘት እያደረገች ያለችውን ጥረት ሩሲያ እንደምትደግፍ ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንቱ በዚሁ ጽሁፋቸው፤ አፍሪካዊያን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት፣ በጂ 20፣ በዓለም አቀፍ የፋይናንስና የንግድ ተቋማት መዋቅር ውስጥ ተገቢውን ቦታ ለማግኘት የሚያደርጉትን ጥረት ሩሲያ እንደምትደግፍ አብራርተዋል።
በዚህ ሳምንት የሚካሄደው የሩሲያ አፍሪካ ጉባኤም ጠቃሚ ውሳኔዎች የሚተላለፉበትና ከዚህ በፊት የተዘጋጀውን የ2026 የአጋርነት የድርጊት መርሀ ግብርም በማጽደቅ የሚጠናቀቅ እንደሚሆን ፕሬዝዳንቱ ያላቸውን ፍላጎትና እምነት ገልጸዋል።
ሩሲያ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ የሚለውን መርህ በጥብቅ እንደምታከብር የገለጹት ፕሬዝዳንት ፑቲን፤ አገራቸው በሌሎች አገራት የውስጥ ጉዳይ ላይም ሆነ አስተዳደራዊና መዋቅራዊ ጉዳዮች ላይ የራሷን ሃሳብ ፈጽሞ እንደማትጭንም ማብራራታቸውን ከኢፕድ ያገኘው መረጃ ገልጿል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia









