
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 17/2015 NBC Ethiopia- የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ዩክሬን ሞስኮ ላይ የሽብር ጥቃት መሰንዘር ጀምራለች ሲል መክሰሱ ተሰምቷል ። የዩክሬን ድሮኖች ዛሬ ማለዳ የሞስኮን ክልል ጥሰው እንደገቡም ታውቋል።
ሆኖም ግን የሩሲያ አየር ሀይል በወሰደው የመከላለከል እርምጃ ድሮኖችን በአየር ላይ እንዳሉ መትቶ መጣሉን እና በሞስኮ ላይ ሊደርስ የነበረውን ጥቃት ማክሸፉን ገልጿል።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ የዛሬው የሰኞ ማለዳ ጥቃት የተፈፀው ሩሲያ በጥቁር ባህር ወደብ ኦዴሳ ላይ ለፈጸመችው ጥቃት ዩከሬን የአጸፋ እርምጃ እወስዳለሁ ማለቷን ተከትሎ ነበር። የዩክሬን ባለስልጣናት ግን በሞስኮ ላይ ተሞክሮ ስለከሸፈው የድሮን ጥቃት ክስ እስካሁን ምላሽ አለመስጠታቸው ታውቋል።
በቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia