በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፍሬው ተገኘ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የተመራቂ ተማሪ ወላጆች፣ የዩኒቨርሲቲው መምህራን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳደር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ተመራቂ ተማሪዎች እና ለተመራቂ ተማሪ ወላጆች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ርእሰ መሥተዳድሩ በመልእክታቸው ባሕርዳር ዮኒቨርሲቱ ላፉት 60 ዓመታት ለሀገር ብቻ ሳይኾን ለዓለም እውቀትን ለማስፋት የሚተጉ፣ ልማትን ለማሳደግ የሚሠሩ፣ የሰውን ሕይወት ለማሻሻል የተጉ ብቃት ያላቸው ሰዎችን በማፍራት አስተዋጽዖ አበርክቷል ብለዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በማስተማር፣ በምርምር እና በማኅበረሰብ አገልግሎት ተልዕኮን ለመወጣት እየሠራ የሚገኝ አንጋፋና ተመራጭ ተቋም ኾኗል ነው ያሉት፡፡
የዩኒቨርሲቲው ተልእኮ የሚሳከው በትጋት በሚተጉ መምህራን፣ ተማሪዎች ትጋትና ተቋርቋሪነት ነውም ብለዋል፡፡
ዮኒቨርሲቲው ለሀገር እያደረገው ያለው አስተዋጽዖ የሚደነቅና የሚበረታታ መኾኑንም ገልጸዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው እውቀትን እያሰፋ፣ ምርምርን እያሳደገ፣ ቴክኖሎጂውን እያስተዋወቀ መኾኑንም ገልጸዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው እስካሁን ተመራጭ ኾኖ የቆየበትን እንደ ስንቅ በመውሰድ በቀጣይም ጠንክሮና አስፍቶ መሥራት አለበት ነው ያሉት፡፡
ዩኒቨርሲቲው ተመራጭ እንዲኾን የሠሩ ሁሉ ወደፊትም በትጋት እንዲሠሩም አሳስበዋል፡፡
ማንኛውም ስኬት የሚገኘው ፈተናን ተጋፍጦ በማለፍ ብቻ ነውም ብለዋል፡፡
ስኬት ዝም ብሎ የሚገኝ እርካሽ ነገር አይደለም፣ መስዋእትነት የሚጠቅይ፣ ያለመሰልቸትና ያለመታከት ሳይደክሙ መሥራትን የሚጠይቅ ተግባር ነውም ብለዋል፡፡
የተማሪዎች ስኬት የዩኒቨርሰቲው ስኬት መኾኑን ገልጸዋል፡፡
ዩንቨርሲቲው ካስመረቃቸው ተማሪዎች በተጨማሪ የሸገር ሬዲዮ መስራችና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያ መዓዛ ብሩ እና የኔዘርላንድስ ተወላጅ ለሆኑት ሄሪት ሆርት የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።



የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ከዚህ ቀደም ለብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ እንዲሁም ለአትሌት ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬት ማበርከቱ ይታወሳል።