
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 14 2015| NBC Ethiopia- የተለያየ ሞዴል ያላቸው የተሰረቁ ቴሌቪዥኖችን እየገዛ ሲያከማች የነበረ ተጠርጣሪ ከነ ኤግዚቢቶቹ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፓሊስ አስወቀ።
ተጠርጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር የዋለው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ሰሚት ኮንዶምኒየም አካባቢ ነው።
ከበሻሌ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ በተገኘው መረጃ መሠረት በህጋዊ የንግድ ፈቃድ ሽፋን የተሰረቁ የተለያየ ሞዴል ያላቸው ቴሌቪዥኖችን ከሌቦች እየተቀበለ እንደሚሸሽግ ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ መሠረት በህግ አግባብ በተደረገ ፍተሻ 17 የተለያየ ሞዴል ያላቸው ከ25 እስከ 65 ኢንች ፍላት እስክሪን ቴሌቪዥኖችን በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ተሰርቆብኛል የሚል ግለሰብ ስለ ንብረቱ ማስረጃ በመያዝና ወደ ፖሊስ ጣቢያው መጥቶ መጠየቅ ይችላል ተብሏል።
ከቅርብ ግዜ ወዲህ በህጋዊ የንግድ ፈቃድ ሽፋን ሀገ-ወጥ ተግባር የሚፈፅሙ ግለሰቦች እየተበራከቱ ስለመጡ ህብረተሰቡ በየአካባቢው ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ለመረጃ ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ፖሊስ አሳስቧል።
በክረምት የአየሩን ሁኔታ እንደምቹ አጋጣሚ ተጠቅመው የስርቆት ወንጀል ለመፈፀም የሚንቀሳቀሱ አካላት ስለሚኖሩ ተገቢውን ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ሲል ፖሊስ መልዕክቱን ማስተላለፉን ኢ.ፕ.ድ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website –https://nbcethiopia.com/news/












