አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 14/ 2015 NBC Ethiopia- የኢራቅ የጸጥታ ሀይሎች ጥቃቱን ማክሸፍ አለመቻላቸው “ተቀባይነት የለውም” ስትል በኢራቅ የሚገኘውን የስዊድን ኤምባሲ ጥቃትን አሜሪካ መቃወሟን አስታውቃለች ።

የስቴት ዲፓርትመንት ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር እንደተናገሩት “የሰላማዊ ሰልፍ ነፃነት የዲሞክራሲ ዋና መለያ ቢሆንም በዲፕሎማቲክ ሚሲዮን ላይ የተፈፀመው ጥቃት “ህገ-ወጥ የሀይል እርምጃ ነው” ብለዋል።
ሚለር በሰጡት መግለጫ “የኢራቅ የጸጥታ ሀይሎች የስዊድን ኤምባሲ ግቢን እንዳይጎዱ ለማድረግ እርምጃ አለመውሰዳቸው ተቀባይነት የለውም ሲሉ ሚለር በመግለጫቸው ተናግረዋል።
“የኢራቅ መንግስት በዓለም አቀፍ ህግ በሚጠይቀው መሰረት ሁሉንም የኢራቅ ዲፕሎማሲያዊ ሚሲዮኖች ከማንኛውም ጣልቃ ገብነት ወይም ጉዳት ለመጠበቅ ያለውን ዓለም አቀፍ ግዴታውን እንዲያከብር እንጠይቃለን” ሲሉም አክለዋል።
የኢራቅ ተወላጅ የሆነው ሳልዋን ሞሚካ ባለፈው ወር በባግዳድ የሚገኘውን የስዊድንን ኤምባሲ በመውረር እ.ኤ.አ በሰኔ 28/2023 ቅዱስ ቁርኣን ቃጠሎን በመቃወም በእሳት አቃጥሏል።

የስዊድን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በባግዳድ በሚገኘው ኤምባሲው ላይ የተፈፀመውን ጥቃት የቪየና ስምምነትን የሚጥስ ነው በማለት ድርጊቱን ኮንኖታል ።
የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር አል-ሱዳኒ በትዊተር ላይ እንዳስታወቁት በባግዳድ የሚገኘውን የስዊድን አምባሳደር ሀገራቸውን ለቆ እንዲወጣ ጥያቄ ማቅረቡን ተናግረዋል ።
እርምጃው የተወሰደው “የስዊድን መንግስት የቅዱስ ቁርኣንን ቅጂ ለማቃጠል፣ የእስልምና ቅዱሳንን ለመስደብ እና የኢራቅን ባንዲራ ለማቃጠል በመፍቀዱ የተሰጠ ምላሽ ነው ተብሏል።
በሃና ተሰማ
ምንጭ(በአናዱሉ)
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc