አዲስ አበባ | ሐምሌ 12 2015 | NBC ETHIOPIA- ከ27 ዓመት በኋላ የአሜሪካ ፖሊስ በኔቫዳ ግዛት ከአቀንቃኙ ቱፓክ ሻኩር ግድያ ጋር በተያያዘ በአንድ መኖሪያ ቤት ላይ ፍተሻ አድርጓል።

ዝነኛ ራፓር የነበረው ቱፓክ በጥይት ተመትቶ ህይወቱ ያለፈው እኤአ 1996 ዓ.ም ላይ ቢሆንም ከግድያው ጋር ተያይዞ በጥርጣሬ እንኳ በቁጥጥር ሥር የዋለ የለም።
ቱፓክ ሲገደል ገና የ25 ዓመት ወጣት የነበረ ሲሆን መርማሪዎች በኔቫዳ ግዛት ከላስ ቬጋስ ከተማ አቅራቢያ ቱፓክ ከተገደለበት ስፍራ አቅራቢያ ያለ መኖሪያ ቤት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ፍተሻ ማድረጋቸውን ከመግለጽ ውጪ ስለፍተሻው ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
የላስ ቬጋስ ፖሊስ በመኖሪያ ቤቱ ላይ ፍተሻ ማድረጉን ይፋ ባደረገበት መግለጫ ከቱፓክ ግድያ ጋር ተያይዞ እየተደረገ ባለው ምርመራና ፍተሻ ማድረጉን ገልጾ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል።
በሃና ተሰማ
ምንጭ(ቢቢሲ)
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook –https://www.facebook.com/ethiopiannbc












