አዲስ አበባ | ሐምሌ 12 2015 | NBC ETHIOPIA- ተጠሪነቱ ለሰላም ሚኒስቴር የሆነውና በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 525/2015 ዓ.ም የተቋቋመው ብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ባከናወናቸው ተግባራትና የመገናኛ ብዙሃን ሚና ምን መሆን አለበት በሚለው ዙሪያ ከሚዲያ አካለት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

በውይይቱም ኮሚሽኑ ከተቋቋመ ስድስት ወራት ውስጥ በስምንት ክልሎች ጋር በተናጠል ውይይት ማከናወኑን ተገልጿል ። የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የሚሰራቸው ስራዎች ላይ ከሚዲያ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት ያለመ ነው ተብሏል።

በመድረኩ በሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ የሚዲያ አካላት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል፡፡
በሰላማዊት ወልደገሪማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website –https://nbcethiopia.com/news/
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc











