የአዲስ አበባን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመቅረፍ እየተከናወኑ ካሉ ተግባራት መካከል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ ተጠቃሽ ነው፡፡
እየተገነቡ ከሚገኙ 5ሺ መኖሪያ ቤቶች 4 መቶ የሚሆኑት በያዝነው ክረምት ለነዋሪዎች እንደሚተላለፍ ክፍለ ከተማው አስታውቋል፡፡
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በተጠናቀቀው ሳምንት 410 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸውን 24 ፕሮጀክቶች አስመርቋል፡፡









