አዲስ አበባ ሐምሌ 7፤ 2015 | NBC ETHIOPIA- ዩክሬን በሩሲያ ላይ የምታደርገውን ቀጣይነት ያለው የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ለማጠናከር የታቀዱ አሜሪካ እና አጋሮቿ ያቀረቧቸው ጥይቶች በጦርነቱ ለምትታመሰው ዩክሬን መድረሱን ፔንታጎን አስታውቀ።

ሌተናል ጄኔራል ዳግላስ ሲምስ እንዳሉት በዩኤስ የሚቀርቡት ጥይቶች በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የ800 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የጦር መሳሪያ በዩክሬን ውስጥ ይገኛል ።
እኤአ በ2008 ዓ/ም ከ100 በላይ ሀገራት ክላስተር ቦምቦችን ማምረት፣ ማከማቸት፣ መጠቀም እና ማስተላለፍን የሚከለክል ስምምነት መፈረማቸው የሚታወቅ ነው ።
የባይደን አስተዳደር ወደ ኪየቭ የሚልካቸው የክላስተር ቦምብ ዓይነቶ በአሁኑ ጊዜ በሩሲያ ከሚገኙት በጣም ያነሰ መሆኑን ይገለፃል።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሩሲያ በዩክሬን ላይ ለጀመረችው ጦርነት ምላሽ የጀመረውን በአውሮፓ እየተካሄደ ያለውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለማጠናከር ወደ 3,000 ለሚጠጉ የአሜሪካ ወታደራዊ ተጠባባቂዎች በር የሚከፍት አዲስ የስራ አስፈፃሚ ትዕዛዝ ፈርመዋል።
በዩክሬን ስላለው ጦርነት የአሜሪካ መረጃ እንደሚያመለክተው የዋግነር ግሩፕ በሩሲያ ወታደራዊ አመራር ላይ ካመፀ በኋላ በአሁኑ ጊዜ ጉልህ እንቅስቃሴ እያደረገ አይደለም ብለዋል።
በሃና ተሰማ
ምንጭ(አናዱሉ)
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc









