
አዲስ አበባ ሐምሌ 6 ፤ 2015 | NBC ETHIOPIA-የሱዳን ወታደራዊ ሀይሎች ጦርነት ሲያካሂዱ ግብፅ ራሷን ለመጠበቅ የምትገደድ ትሆናለች ስትል ትናገራለች ። ግብፅ ይሄን ስጋት ለመቀነስ በሱዳን ላይ የተለያዩ ወታደራዊ እና ሲቪል ቡድኖችን እንዲሁም በችግሩ ውስጥ ያሉ የሀገሪቱ ጎረቤቶች የሚሳተፉበት ስብሰባ እንደምታዘጋጅ የተነገረ ሲሆን ይህም ሀሙስ ሀምሌ 13 / 2023 ዓ/ም በካይሮ ይጀመራል ተብሏል።
ጉባኤው የሱዳንን ሰላም ወደቀድሞ ቦታው ለመመለስ ውጤታማ ዘዴዎችን ለማዘጋጀት ያለመ ነው ። በሱዳን የቀጠለው ጦርነት በግብፅ ላይ ምን ያህል ስጋት እንዳለው በመገንዘብ፣ ካይሮ ይህንን እድል ተጠቅማ ደቡባዊ ጎረቤቷን ለማረጋጋትን ከባድ አለት መፈልፈል አንደሚኖርባት ያመነች ይመስላል። ስትራቲጅካዊ እና ፖለቲካዊ ዳረንጎት ለመውሰድ የምትቋምው ካይሮ አሁን የተከሰተው የሱዳን ግርግር በወደፊት ትኩስ እንጎቻዋ ላይ አመድ መነስነስ መስሎ ሰለታያት መቀመጫና መቆሚያ ያጣውን የሱዳን ጉዳይ ሳይውል ሳያድር መፍትሄ ማግኘት ይኖርበታል ብላ አስባለች ለዚህም ስብሰባ ጠርታለች ምናልባት አማላጅ ከተገገኘ በሚል ይሆናል፡፡ ሊቢያ፤ ቻድና ሱዳን የካይሮ ድንበርተኞች በመሆናቸው እና በዚህ አካባቢ ከባድ መፈናቀል ስለሚከሰት ወደ ግዛቷ የሚፈልሰውን ሰው ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ከመሆኑ በፊት በአንድ ጀምበር መቋጨት ግድ ሆኖባታል፤፤
የሱዳን ወታደራዊ ሀይሎች እርስበርስ ለስልጣን ሲፋለሙ ለሶስት ወራት የዘለቀው ግጭት ለግብፅ ከድንበር ደህንነቷ፣ ግዛታዊ አንድነቷ፣ሉዓላዊነቷ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዋ ጋር የተያያዙ ብዙ ስጋቶች አሉባት። ለካይሮ ሌላ የክንፍ ጉረቤት የሆነችው ሊቢያ በሰላም እጦት እየታመሰች የምትገኝ በመሆኗ የፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ ኤል-ሲሲ መንግስት በሱዳን ያለውን ቀውስ ሌላ ራስ አፍርስ በሽታ በመሆኑ በጊዜ ካልተፈታ ክሩ ለሌላ ጥምጥም ፈተና እንደሚዳርግ የጠረጠሩ ይመስላል።
የግብፅ መሪዎች ጦርነቱ ከካይሮ አቅራቢያ በተቻለ መጠን እንዲርቅላቸው ቆርጠው ተነስተዋል ምክንያቱም መንግሥታዊ ያልሆኑ ተዋናዮች የሱዳንን ቀውስ በማሳበብ ግብፅን ስጋት ውስት ሊጥሉ ይችላሉ ተብለው የሚጠረጠሩ ሀይሎች ይኖራሉ።

እ.ኤ.አ. ከ2011 ከግብፅ አብዮት ጀምሮ ሱዳን ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ካላቸው ቡድኖች ጋር ወደ ግብፅ የሚሻገሩ ጥቃቶች እና እንዲሁም ህገወጥ የሰዎች ዝውውር እንደ ተጨማሬ ፈተና በመሆኑ ነው ፣ ስለዚህ የካይሮን ደቡባዊ ድንበር በወታደራዊ ሀይል አጥብቆ መጠበቅ የግድ ይሆናል ።
በአትላንቲክ ካውንስል ከፍተኛ ባልደረባ የሆኑት አሌሲያ ሜልካንጊ በደህንነት ደረጃ፣ የግብፅ መንግስት በድንበር አካባቢ የሽብር ጥቃት ስጋት አለበት ፤ ይህ ሁኔታ አስቀድሞ ከሊቢያ ምዕራባዊ ድንበር ላይ እና የሲና ባሕረ ገብ መሬትን ለመከላከል ከጋዛ ሰርጥ ጋር ድንበር ስለሚጋራ የግብፅ የጸጥታ ኃይሎች ላይ ተጨማሪ ጫና ይፈጥራል በማለት የግብፅን ስጋት ይጋራሉ::
የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ግብፅ በጠራችው ስብሰባ ላይ ስለመገኘታቸው የታቀወቀ ነገር እስካሁን የለም። ከዚህ በተጨማሪ አዲስ አበባ በነበረው የኢጋድ ስብበሳ ላይ ሳይገኙ ከቀሩት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ውጪ የትኞቹ የቀጠናው ሀገራት መሪዎች እንደሚገኙ እሰካሁን በይፋ የተባለ ነገር ባይኖርም ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ግን ዛሬ ሀምሌ 13/ 2023 ወደ ግብፅ አቅንተዋል ። ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ አሜሪካ እና ሳዑዲ አረቢያ በጂዳ ሁለቱን የጦር ጄኔራሎች ለማግባባት ጥረት ሲያደርጉ ካይሮ እና አቡ ዳቢ ተሳታፊ እንዳልበሩ የሚታወስ ነው ፡፡
ከዚህ ቀደም ግጭት ውስጥ የገቡትን የሱዳንን ጦር ሠራዊት አዛዥ ጄኔራል አብደል ፋታህ አል ቡርሐን እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መሪ የሆኑትን ጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ዳጋሎን ለማግባባት የተደረጉ ተደጋጋሚ ጥረቶች ቢደረጉም መሬት ሳይነኩ ቀርተዋል፤ ፍሬም አላፈሩም።
አሜሪካ እና ሳዑዲ አረቢያ ተፋላሚ ኃይሎቹ በተደጋጋሚ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደርሱ ማድጋቸው ቢገልጽም ይህ ተግባራዊ ሳይሆን ውጊያው ቀጥሏል። ሶስት ወር ሊደፍን የተቃረበው ግጭት በተለይ የሱዳን መዲና ካርቱም ነዋሪዎችን ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ከትቶ ይገኛል። ሁለቱም ኃይሎች ዋና ከተማዋን ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥራቸው ስር ለማስገባት እየተፋለሙ እንደሆነም እተሰማ ነው።
የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የካርቱምን፣ የኦምዱርማንን እና የባህር ዳርቻ ከተሞችን አብዛኞቹን ክፍሎች በቁጥጥሩ ስር አድርጎ ይገኛል። የእርስ በርስ ጦርነቱ ወደ ሶስት ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብን ከመኖሪያው ያፈናቀለ ሲሆን፣ ስባት መቶ ሺህ የሚሆኑት ደግሞ አገር ጥለው መሰደዳቸው በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋመት የሚወጡ መረጃዎች ያመለካታሉ።
የሱዳን ቀውስ ወደ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የመዛመት ዕድሉ ሰፊ ይሆናል የሚለው ጥርጣሬ ለኤል-ሲሲ መንግስት ተስፋ አስቆራጭም ነው። በአረብ ሴንተር ዋሽንግተን ዲሲ የጥናት አባል ዳይሬክተር የሆኑት ኢማድ ሃርብ ከአልጀዚራ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ “ካይሮ በካርቱም ካለው ግጭት ምንም አይነት መዘዝ እንዲመጣባት አትፈልግም” ብለዋል። ከሁሉም በላይ ግን በቻድ እና በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ያለው ግጭት መራዘሙ ለግብፅ ባለስልጣናት የጸጥታ ችግሮችን ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት ነው ካይሮን ረፍት የነሳት ይላሉ ምሁሩ።
ከሚያዝያ አጋማሽ ጀምሮ ወደ 256,000 የሚጠጉ ሱዳናውያን ስደተኞች ግብፅ ገብተዋል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ሱዳናውያን በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ ወደ ግብፅ ሊመጡ ይችላሉ የሚለው ስጋት የካይሮ መንግስት ሊደርስበት የሚችለውን የገንዘብ ጫና ካሁኑ በመፍራት የሱዳንን ችግር በቶሎ መቋጨት እንቅልፍ የማያስወስድ ሆድ ህመም ነው፡፡ ስለዚህ በፍጥነት የሱዳን ግጭት መፍትሄ ማግኘት የግድ ይኖርበታል በማለት የፖለቲካ አዋቂዎች ይናገራሉ ።
በቶማይ መኮንን
ምንጭ (አልጀዚራ)
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook-https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት











