
አዲስ አበባ ሐምሌ 5 ፤ 2015 | NBC ETHIOPIA- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዶ/ር በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳስታወቁት ከግቡፁ ፕሬዝደንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ጋር በግብፅ ካይሮ መክረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በግብጽ ካይሮ ከፕሬዚዳንት አብዱልፈታሕ ኤልሲሲ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ትብብር በሰፈነበት መንፈስ ውይይቶች አካሂደናል።” ሲሉም ነው የገለጹት።

በውይይታቸውም የሁለትዮሽ ትብብር ጉዳዮች እንዲሁም ወቅታዊ የቀጠናው ሁኔታዎች መነሳታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc












