
አዲስ አበባ ሐምሌ 5 ፤ 2015 | NBC ETHIOPIA- ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን፣ ጆ ባይደን በሊትዌኒያ ከኔቶ መሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ተገናኝተው ተወያተዋል።
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን እና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ የጸጥታ ትብብር እና ቀጠናዊ ጉዳዮችን ጨምሮ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮችን ከኔቶ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ተወያይተዋል።
የሁለትዮሽ ግንኙነታችን አዎንታዊ ውጤት እንደሚያመጣ ያላቸውን ተስፋ በትዊተር ገፃቸው ኤርዶጋን የገለፁ ሲሆን “በስብሰባችን ወቅት በጸጥታ መስክ ላይ ስላለው የትብብር አማራጮች ተወያይተናል” ብለዋል።
31 ቱ የኔቶ መሪዎች የዩክሬን ጦርነት፣ የስዊድን የኔቶ አባልነት እና የቡድኑን መከላከያን ለማጠናከር በሚወስዱት እርምጃዎች እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ለመምከር ለሁለት ቀናት በሊትዌኒያ ዋና ከተማ ቪልኒየስ ለሁለት ቀናት የመሪዎች ስብሰባ አድርገዋል፡፡
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facbook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












