
አዲስ አበባ ሐምሌ 4 ፤ 2015 | NBC ETHIOPIA -የሰሜን የጦር ቃልኪዳን ድርጅት መሪዎች በዩክሬን ጦርነት ዙሪያና እና በምዕራባውያን አንድነት የወደፊት ህልውና ላይ ለመምከር በሉቱዌኒያ እየተገናኙ ነው መሆኑ ታውቋል።
ሰላሳ አንድ የሚሆኑት የኔቶ አባላት የዩክሬንን ጦርነት በተደራጀ መልኩ ለመርዳት ሀሳብ እንዳለቸውም እየተገለፀ ነው፡፡
ኪዬቭ በበኩሏ ሩሲያ የምታደርግባትን ወረራ ለመከላከል አዲስ የጸጥታ ዋስትና እንደምታገኝ በኔቶ ስብሰባ ላይ ተስፋ አድርጋለች ተብሏል፡፡
የዩክሬኑ ፕሬዚደንት ዜለንሰኪም፣ በተቻለ ፍጥነት ሀገራቸው ህብረቱን መቀላቀል እንደምትችል ኔቶ እንዲፈቅድላት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የኔቶ ዋና ጸሐፊ ጀንስ ስቶልተንበርግ፣ በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ አለመሰጠቱን ገልጸው ነገር ግን ህብረትና ለዩክሬን ጠንካራ መልዕክት እንደሚኖር ተናግረዋል።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው ጉባኤ የኔቶ መሪዎች በምሥራቅ አካባቢ የሚገኙ አባላቶቻቸውን በማጎልበት ሀገራቱን ከወደፊት የሩሲያ ጥቃት ለመከላከል የሚረዳ አዲስ ስልቶች ላይ ከስምምነት ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል ።
በቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia