
ሆሊዉድ ሩሲያን የተወዉ ከአንድ አመት በፊት ነዉ ። ነገር ግን የሀገሪቱ box office አሁንም ሪከርድ እያስመዘገበ ነዉ። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?
ባለፈዉ አመት ብዙ የምዕራባዉያን ኩባንያዎች ሩስያን ለቀዉ ወጥተዋል። ይህም በኢኮኖሚው ላይ ብቻ ሳይሆን የባህል ገፅታዉንም ለዉጧል። የፊልም ኢንዱስትሪዉም ከዚህ የተለየ አይደለም። በዚህም ሀገሪቷ ያለ ምዕራባውያን አገልግሎት ለፊልም ንግድ ያላትን አቀራረብ እንደገና እያጤነች ነዉ።
ሩስያ በጣም ብዙ ተነሳሽነትን የሚፈጥሩ ምሳሌ የሚሆኑ ስራዎች አሏት። በብዙ ቦታ የብሄራዊ ሲኒማዉ በ box office የመሪነትን ቦታ ይይዛል።
የተለያዩ ሀገሮች የፊልም ኢንዱስትሪዎቻቸውን በተለያየ መንገድ ገንብተዋል። አንዳንዶቹ በሀገር ዉስጥ ተመልካቾች ያተኮሩ ሲሆን ሌሎች ደግሞ በመንግስት የተደገፋ ሆነዉ በሀገር ዉስጥም ከሀገር ዉጪ ያሉ ተመልካቾች ላይ ትኩረት አድርገዉ ይሰራሉ። በተጨማሪም ከአለም አቀፍ የፊልም ታዳሚዎች ጋር የሚስማሙ ስራዎችን ያስተላልፋሉ።
ታዲያ እነዚህ ሀገሮች ከ Hollywood ወጪ እንዴት ሆኑ?
ሩሲያስ ባለፈዉ አመት በዚህ ርቀት ምን ያህል ተጉዛለች?
ምንድን ነዉ የተፈጠረዉ?
ከ February 24 በኃላ ባለፈዉ አመት ብዙ የምዕራባውያን የምርት ኩባንያዎች የሩስያ ቢሮዎቻቸውን ዘግተዉ ከተለያዩ ስቱዲዮዎች ጋር ኮንትራታቸዉን አቋርጠዋል። Paramount pictures እና Warner Bros., Netflix እና Amazon Prime, Marvel እና Disney ሁሉም በሩስያ ዉስጥ ፊልሞችን መልቀቅ አቁመዋል። መድረኮቻቸዉንም አግደዋል።
ይህ ዉሳኔ በፊልም ኢንዱስትሪው ሆነ በተመልካቾች ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ያሳድራል። ከ Netflix ጋር ያሉ የጋራ ፕሮጀክቶችም ላልተወሰ ጊዜ ቆመዋል። ከዚህ በፊት አለማቀፍ መድረክ the epidemic and the method ተከታታይ ፊልሞችን ከሩስያ በመግዛት የራሱን ይዘት ለማምረት አቅዶም ነበር። በአለም አቀፍ ደረጃም ከፍተኛ ገቢ ያስገኙ እንደ Batman እና the gun maverick ፊልሞች በሩስያ ዉስጥ እንዳይገኙ ሆነዋል።
ከአሜሪካ ተንቀሳቃሽ ምስል ኩባንያዎች ጋር በርካታ የምዕራብ አዉሮፓ ስቱዲዮዎች ሩስያን ለቀዉ ወጥተዋል። ይሁን እንጂ በአንድ አመት ዉስጥ ከአሜሪካ አቻዎቻቸዉ ይልቅ በሩስያ ገበያ ላይ ጥገኛ መሆናቸዉ ግልፅ ሆኖአል።
አንድ ምሳሌ በታህሳስ መጀመሪያ ላይ ተመልሶ እንደሚመጣ ያሳወቀዉ የፈረንሳይ የፊልም ኩባንያ ፓቼ ነዉ።
ላለፉት አስርት አመታት ሩስያ በአለምአቀፍ የፊልም ገበያዉ ላን ንቁ አካል ሆናለች። Balagov and Ilya Naishuller, ያሉ የሩስያ የፊልም ዳሬክተሮች በአለምአቀፍ የፊልም ፕሮጀክቶች ዉስጥ በትልቅ በጀት ተሳትፈዋል። የሩሲያ ተከታታይ ፊልሞች ብዙ ተመልካቾችን አግኝተዋል። ለምሳሌ the epedmic የተሰኘዉ ፊልም በNetflix ብዙ እይታን አትርፏል።
የፓለቲካ ልዩነቶች የሩስያን የፊልም ኢንዱስትሪ ወደ አንድ እዉነታ እያመጣዉ ይገኛል። በዚህም ኢንዱስትሪዉ የተለያዩ ባህል ላይ ያተኮሩ ስራዎችን ለመስራት እና ለማሰራጨት በድጋሚ እየቃኘዉ እንደሆነ ተነግሯል። በዚህም ከ Hollywood በላይ እንዴት መስራት እንደሚችሉ ምርምር እያረጉ ነዉ።
በዋናነት ግን Hollywood ለምንድን ነዉ የአለም ፊልም ኢንዱስትሪ የሚቆጣጠረው?
ሆሊውድ የተለየ ኢንዱስትሪ ነዉ። ዘመናዊ የሆኑት ፊልሞችን ለአለም አቀፍ ተመልካች የተበጁ ናቸዉ። ዋናዉ አላማዉም ተመልካችን ማብዛት ነዉ።
ሆሊዉድ ለምን የአለም የፊልም ገበያ እንደሚቆጣጠር የተለያዩ ምክናያቶች እና አመለካከቶች አሉ። united States ብዙ የህዝብ ቁጥር አለ እንዲሁም የሀገር ወስጥ ገበያዉ በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ የሚሰሩ ፊልሞች ወደ ሀገር ዉስጥ በመመለስና በድጋሚ በመላክ ከሀገር ዉስ ፊልሞች ጋር ይወዳደራሉ። እንደነዚህ አይነቱ ስልት የተለያዩ አደጋዎችን ያስወግዳል። ዉድቀት ቢኖርም የገንዘብ ኪሳራ ግን ሊደረስበት አይችልም። ከዚህም በላይ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኃላ የ US ኢኮኖሚ እድገት ለፊልም ኢንዱስትሪው መጠናከር አስተዋጽኦ አድርጓል ።
ይሁን እንጂ ሆሊውድ ሁሉንም ገበያዎች መቆጣጠር አልቻለም። እንደ ህንድ ቻይና እና አፍሪካ ባሉ ከፍተኛ የባህል ልዪነት ባለባቸዉ ሀገሮች የአሜሪካ ፊልሞች ድርሻ አነስተኛ ነዉ።
በ2022 የመጀመሪያ አመት ላይ የተሰሩ የሩስያ ፊልሞች ቦክስ ኦፊስ ላይ 52.1% ደርሻ እንዲኖረዉ አድርገዉ ነበር። በ January 2023 የሩሲያ ሲኒማ ከምንጊዜውም በላይ መሻሻል የታየበት ሆኖአል። በዚህም የቦክስ ኦፊስ ገቢዉ 8663 billion ገቢ ደርሷል። ይህም ከ 2022 የ 61.8% ጭማሪ ሲኖረዉ በ 2020 የተቀመጠዉን ሪከርድ በ 12.3% አሻሽሏል።
ይህ ስኬት የተመዘገበዉ family blockbuster “Cheburashka” የተሰኘዉ ፊልም በመሀቀቁ ነዉ ይህም በብሄራዊዉ box office ከ avatar የተሰበሰበዉ 80million dollar የሚበልጥ ነዉ።
በአሁን ወቅትም ሪከርዱን ባይሰብሩም ስኬታማና ሊወደዱ የሚችለሉ የተለያዩ ፊልሞች በመሠራት ላይ ናቸዉ። ለምሳሌ ያክልም The challenge የተሰኘዉ ፊልም April ላይ ይለቀቃል ይህም በ ISS በጠፈር ላይ የተቀረፀ የመጀመሪያ ፊልም ነዉ።
የሆሊዉድ አለመኖር የሀገር ዉስጥ ፊልሞች ላይ እድገት በማምጣ ሚዛናዊ እንዲሆን አድርጎታል። እ.አ.አ በ 2022 መገባደጃ ላይ ወደ ገበያው የገቡት የሩስያ ፊልሞችም ና ተከታታይ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ብዛት በ 16 በመቶ ጨምሯል።
ይህ እድገት የተቀሰቀሰዉ ሆሊውድ blockbuster ችን በማቋረጡ ሲሆን ለመመለስ ካሰበ ሆሊውድ ከባድ ፉክክር ሊገጥመዉ ይችላል ተብሏል።
በሊያ ክብሮም
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት









