
አዲስ አበባ |የካቲት 17 2015 | NBC ETHIOPIA-አመጋገባችን ለሰዉነታችን እንዲሁም ለአዕምሮአችን ጠቃሚ እንደሆነ እሙን ነዉ። የምንመገባቸዉ ምግቦች በዉስጣቸዉ የያዙትን ንጥረነገሮች ማወቅ ደግሞ የትኛዉን ከየትኛዉ ጋር እንደሚሄድና በምን መልኩ ማብሰል እንዳለብን እንድናዉቅ ይረዳናል።
ለዛሬ በምንመገባቸዉ ምግቦች ዉስጥ በመቀላቀል እንደተጨማሪ ግብዐት በመጠቀም እንዲሁም ለብቻቸዉ ብንመገባቸዉ ጠቃሚ የሆኑትን የአትክልት አይነት እናጋራችሁ።
የመጀመሪያዉ ብሮክሊ ነዉ። ብሮክሊ ለጤና የሚሰጠዉ ጥቅም እጅግ ከፍተኛ ነዉ። ብሮክሊ በፋይበር ቫይታሚን ሲ ቫይታሚን ኬ እና ፓታሺየምን ጨምሮ በሌሎች ንጥረነገሮች የበለፀገ ነዉ። እንዲሁም ከሌሎች አትክልቶች በበለጠ በፕሮቲን የበለፀገ እንደሆነ ይነገራል ስለዚህ ለህፃናት ዕድገትን ሲያፋጥን ሰዉነት በመገንባትም ትልቅ አስተዋፅዖ አለዉ።
በዚህም ብዙ የሚሰጠዉ ጠቀሜታ አለ። የስነምግብ ባለሙያዎች እንደሚሉት ብሮክሊ በ ፋይበር የበለፀገ ስለሆነ የምግብ መፈጨትን ያፋጥናል እንዲሁም ኮሌስትሮልን በመቀነስ የልብን ጤንነት ይጠብቃል።
በዉስጡ ባሉት ንጥረነገሮች የደም ግፊትን ይቆጣጠራል። በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራል። የአንጎል ና የነርፍ ስርዐትን ይቆጣጠራል። ቁስለትና እብጠትን በቶሎ ለማዳን ይጠቅማል።
ብሮክሊን ለብቻዉም ሆነ ከሌሎች ምግቦች ጋር ከአትክልት፣ ከሩዝ፣ ከፓስታ፣ ከመኮሮኒ ጋር በመቀላቀል መኘገብ ይቻላል። ለልጆችም በምንሰራቸዉ ምግቦች ዉስጥ በመቀላቀል መመገብ ይቻላል።
በቀጣይ የምናልፈዉ በርካታ ጠቀሜታ ስላለዉ ዝኩኒ ነዉ። ዝኩኒ ለጤና ከመጥቀሙም ባሻገር በጣዕሙ ተመራጭ
ነዉ። በቫይታሚኒና በሚኒራል የበለፀገ ነዉ። ዝኩኒ ካሉት የጤና በረከቶቹ ዉስጥ ጥቂቶቹ
– የአይን ጤንነትን ለመጠበቅ ይረዳል
– የሰዉነት ክብደትን ይቆጣጠራል
– ካንሰርን ይከላከላል
– ቆዳ እንዳያረጅና እንዳይጨማደድ ያደርጋል
– በሪህ በሽታ የመያዝ ዕድልን ይቀንሳል
– የፀጉር እድገትን ያፋጥናል።
ዝኩኒን እንደሁሉም አትክልት ለብቻዉ መመገብ እንችላለን። በተጨማሪም ከእንቁላል ጋር በሠጥበስ ከሌሎች አትክልቶች ጋር በመቀላቀል እንዲሁም በየዕለቱ ከምንመገባቸዉ ምግቦች ጋር በመቀላቀል መጠቀም እንችላለን።
በመጨረሻም የአበባ ጎመንን እናንሳ። የአበባ ጎመን በንጥረ-ምግብ ይዘት ከሌሎች የጎመን ዓይነቶች መካከል መሪ እንደሆነ ይታወቃል።
በአበባ ጎመን ውስጥ የሚገኙት ቫይታሚኖች በሰው አካል ላይ በጣም ጠቃሚ ውጤት አላቸው። ጥሩ የተፈጥሮ አንቲኦክሲደንት አለዉ። ማንኛውንም በተፈጥሮ የሚመጣ እብጠትን ለመዋጋት ይረዳል።
የቫይታሚን እጥረት መከሰትን ይከላከላል በተጨማሪም የተከማቹ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ከሰውነት ያስወግዳል።የዓይን ጤናን ይከላከላል። የደም ሥሮች ያጠናክራል እንዲሁም የልብ ሕመምን ይከላከላል።
የምግብ መፈጨት ሥርዓት, የአንጀት እንቅስቃሴን ይቆጣጠራል. በአበባ ጎመን አበባዎች ውስጥ እንደ ግሉካራፊን ያለ ንጥረ ነገር ተገኝቷል። በጨጓራ በሽታ የመያዝ እድልን ይቀንሳል። ብዙ ብዙ ጥቅሞችን ማንሳት ይቻላል።
የአበባ ጎመንን በብዙ መንገድ መጠቀም ይቻላል። ከሾርባ ጋር ከተለያዩ አትክልቶች ጋር በመቀላቀል በተጨማሪም ለህፃናት ብዙ ጥቅሞችን ስለሚሰጥ እነሱንም መመገብ መልካም ነዉ።
ከላይ የተጠቀሰሱትን አትክልቶች ስንመገብ በደንብ ማጠብ ልንረሳዉ የማይገባ ጉዳይ ነዉ።
በሊያ ክብሮም
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት









