፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 02 2016| NBC ETHIOPIA-የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሐረሪ ክልል የሚያከናውነውን የአጀንዳ ማሰባሰብያ መድኩን ነሐሴ 4 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚጀምር በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቋል፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር መሀመድ ድሪር ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ በሀረሪ ክልል በሚከናወነው የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮች፣ የተለያዩ ተቋማት እና ማህበራት ተወካዮች፣ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሶስቱ የመንግስት አካላት ተወካዮች እንዲሁም ታዋቂ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በመሳፍ አጀንዳዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል፡፡

መድረኩ ለተከታታይ ስድስት ቀናት የሚከናወን ሲሆን 1 ሺህ ዜጎችን እንደሚያሳትፍ ተነስቷል፡፡
የአጀንዳ ማሰባሰቢያ የውይይት መድረኩ የተሳካ እንዲሆን ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












