፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 26 2016| NBC ETHIOPIA-የሊባኖሱ ተዋጊ አንጃ ሄዝቦላ በእስራኤል ላይ ከባድ የተባለ የሮኬት ጥቃት መፈፀሙ ተሰምቷል፡፡
እስራኤል ሰሞኑን በፈፀመችው ከባድ ጥቃት የሊባኖሱን ከፍተኛ መሪና የሀማሱን የፖለቲካ ቢሮ ሀላፊውን ኢስማይል ሀኒያን መግደሏ ይታወቃል፡፡ ያንን ተከትሎ ሄዝቦላ በሰሜናዊ እስራኤል ከስልሳ በላይ ሮኬቶችን ማስወንጨፉ ተነገግሯል፡፡

የእስራኤሉ የህዝብ ሬዲዮ ካን ባሰራጨው ዘገባ ሄዝቦላ ካስወነጨፋቸው ስልሳ ሮኬቶች አስራ አምስቱ በአየር ላይ መምከናቸው ነው የተገለፀው፡፡
ከዚያ ውጭ ሌሎች ሮኬቶች በሙሉ ሰው በሌለበት ባዶ መሬት ላይ ማረፋቸውን የእስራኤሉ ካን ሬድዮ ዘገባ ያስረዳል። የእሰሰራኤል ጦር ሀይል ማክሰኞ ዕለት በፈፀመው የአየር ጥቃት የሄዝቦላውን ከፍተኛ አዘዥ ፈአድ ሹኩርና ሌሎች ሰባት ሰዎችን መግደሉ ይታወሳል ዘገባው የአናዶሉ ነው፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












