፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 04 2016| NBC ETHIOPIA- የዩጋንዳ ምክር ቤት የሀገሪቱን ፕሬዝዳንትና ቤተሰባቸውን በቲክ ቶክ ተሳድቧል ያለውን የ24 ዓመት ወጣት የስድስት ዓመት እስራት መፍረዱን አስታወቀ።

ኤድዋርድ አው-ብዋ የተባለው ወጣት በዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩሬ ሙሲየቬኒ ባለቤት ቀዳሚዊት እመቤት ጃኔት ሙሲየቬኒ እና የሀገሪቱ ወታደራዊ አዛዥ በሆነው ልጃቸው ሙሆዚ- ካኔሩ- ጋባ ላይ የጥላቻ እና አሳሳች ንግግርን በማሰራጨት ወንጀል ተከሶ ፍርድ ተላለፍበታል ተብሏል፡፡
ፍርድ ቤቱ በተከሳሹ ላይ ሙሲየቬኒ የግብር ጭማሪ ሊያደርጉ ነው በሚል የተላለፈውን መረጃ ተመልከቶ ውሳኔ እንደሰጠ ተመላክቷል፡፡ተከሳሹ ጥፋተኛነቱን በመቀበል ይቅርታ ጠይቋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በ- ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
Facebook –https://www.facebook.com/ethiopiannbc












