፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 30 2016| NBC ETHIOPIA- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በማያናማር ንጹሀን ላይ የደረሰውን ጥቃት ማውገዛቸው ተገለጸ፡፡
የመብት ተሟጋቾች የማያናማርን ወታደሮች ወደ 70 በሚደርሱ ንጹሀን ላይ የፈጸሙትን ወንጀል ኮንነዋል፡፡
የሀገሪቱ መንግስት ክሱ መሰረተ ቢስና የኤኤ ታጣቂ ቡድን ፕሮፖጋንዳ ነው ሲል አጣጥሎታል፡፡ በምዕራብ ራኪን ግዛት የሚንቀሳቀሰው የኤኤ ታጣቂ ቡድን በመንግስት ወታደሮች ላይ ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ ነው ግጭቱ የተቀሰቀሰው ፡፡

የኤ. ኤ ታጣቂ ቡድን በምዕራብ ማያናማር ለሚገኙት ራኪን ጎሳዎች እና 6 መቶ ሺህ ለሚሆኑ ለስደተኛ ሮሂንግያ ዜጎች ነጻነት እንደሚዋጋ ይገልጻል ፡፡
ጉተሬዝ የሮሂንግያ ዜጎች በመንግስትና በታጣቂ ቡድኖች ተደጋጋሚ እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን ገልጸው፤ ሁለቱ ሀይሎች የተኩስ አቁም ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል ፡፡
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የሮሂንግያ ጎሳዎች የባንግላዴሽ ጉረቤት ወደሆነችው ራኪን በ2017 እንደተሰደዱ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ዘገባው የቲ አር ቲ ቲ አር ቲ ወርልድ ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












