Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

በህንድ የተከሰተው ከፍተኛ የሙቀት መጠን

May 15, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

ለ42 ቀናት የሚቆውና የአለማችን ግዙፉና ውዱ ምርጫ በማድረግ ላይ የሚገኙት ህንዳውያን በከፍተኛ ሙቀት እየተጠቁ ነው ሲል አልጀዚራ ዘግቧል፡፡ በህንድ በተከሰተው ከፍተኛ ሙቀት በመካሄድ በሚገኘው ምርጫ ላይ ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑንም ዘገባው አያይዟል፡፡

ከፍተኛ የሙቀት መጠኑ በመራጮች ተሳትፎ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንዲሁም የመራጮችን ስሜትን ሊያናውጥ ይችላል የሚሉ ጥናቶችም እየወጡ ነው፡፡ አንዳንድ የምርጫ እጩ ተወዳዳሪዎችም በሙቀቱ ሳቢያ ራሳቸውን እስከመሳት መድረሳቸውን አልጄዝራ ዘግቧል፡፡

በማዕከላዊ ህንድ የመንገድ ትራንስፖርት ሚኒስትር የምርጫ ቅስቀሳ ላይ እንዳሉ ድንገት ራሳቸውን ስተው መወውደቃቸው የተገለፀ ሲሆን ከፍተኛ ሙቀት መጠኑም ምክንያት መሆኑን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

የሀገሪቱ የሚትሪዎሎጂ ኤጀንሲ ቀደም ሲል በግንቦት የሙቀት መጠኑ ከመደበኛው በላይ ሊሆን ይችላል ሲል አስጠንቅቆ የነበር ሲሆን በደቡብ ራጃስታን፣ ምዕራብ ማድያ ፕራዴሽ እና ጉጃራት የሙቀት መጠኑ ከመደበኛ በላይ ሆኖ ተመዝግባል፡፡

በዚህም በምስራቃዊ ህንድ አማካይ የሙቀት መጠን በሚያዝያ ወር 28.12 ዲግሪ ሴልሺየስ የነበረ ሲሆን በተያዘው ወር ግን የሙቀት መጠኑ 45 ዲግሪ ሴልሺየስ መድረሱን መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

የሀገሪቱ 970 ሚሊዮን መራጮች ፣ 15 ሚሊዮን የምርጫ አስፈፃሚዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ እጩዎች ከከባዱ የበጋ ወቅት ጋር እየታገሉ ምርጫውን   እያካሄዱ ነው። ነገር ግን መራጮች በጎዳናዎች በሚደረጉ የፖለቲካ ዝግጅቶች ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ መርሃ ግብራቸውን ሊያስተካክሉ ግድ ብሏቸዋል፡፡ በዚህም የምርጫ ቅስቀው ወደ ማለዳ እና ምሽት ቀይረውታል የተባለው ሲሆን የምርጫ ቅስቀሳ በሚደርጉበት ወቅትም ዣንጥላ፣ ኮፍያ እና የመጠጥ ውሃ እንዲይዙ ግድ ሆኖባቸዋል ፡፡ ሙቀቱ የማይቻል ነው፤ በጠራራ ፀሀይ ቅስቀሳ ማድረግ እጅግ ከባድ ሆኗል ሲሉም እጩ ተወዳዳሪዎችና መራጮች ተናግረዋል፡፡

የሕንድ አጠቃላይ ምርጫ በየአምስት ዓመቱ በሚያዝያ እና በግንቦት የሚካሄድ ሲሆን መራጮች እና የምርጫ አስፈፃሚዎች ኃይለኛውን የበጋ ሙቀት ለመቋቋም ይገደዳሉ፡፡ ነገር ግን በዘንድሮ የተከሰተው የሙቀት መጠን ከቅርብ ዓመታት ብሎም ከሌሎች የእስያ ክፍሎች ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግባል፡፡ ባሳለፍነው ሚያዝያ በሀገሪቱ በተመዘገበው ከፍተኛ የሙቀት መጠን ቢያንስ 9 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ይታወሳል፡፡

የምርጫ አስፈፃሚዎች ሙቀቱን ለመቋቋምና በሰዎች ላይ ጉዳት እንደይከሰት  በምርጫ ጣቢዎቸ ውስጥ የመጠጥ ውሃ በማቅረብ እና የምርጫ ጊዜያትን በማራዘም እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው ተብሏል።

የዘንድው ምርጫ ከ2019 ምርጫ ጋር ሲነጻጸር ሚያዝያ 19 እና 26 የተካሄዱት የመጀመሪያዎቹ ሁለት የምርጫ ደረጃዎች እያንዳንዳቸው ቢያንስ 3 በመቶ መራጮች ብቻ ተሳታፊ መሆናቸውን ተገልፃል፡፡ የተመዘገበው ከፍተኛ ሙቀት ለመራጮች ተሳትፎ መቀነስ ምክንያት መሆኑን የፖለቲካ ተንታኞች ጠቅሰዋል።

ከግንቦት 16 ጀምሮ በፑንጃብ፣ ኡታር ፕራዴሽ እና ሃሪያናን ጨምሮ በሰሜን ምዕራብ ክልል አዲስ የሙቀት ማዕበል ሊከሰት እንደሚችል የህንድ ሜትሮሎጂ ዲፓርትመንት አስታውቋል፡፡

የሙቀቱ ተጽዕኖ በምርጫው ሂደት ላይ ብቻ ሳይሆን የውሃ እጥረት፣ የሰብል መጎዳት እና የሃይል ፍላጎት ከፍ በማድረግ የሃይል እጥረት እንዲከሰትም ምክንያት ሆናል በሚል ቅድመ ትንቤ ተቀምጧል፡፡ በሀገሪቱ ከመደበኛ በላይ የሆነው የሙቀት መጠን በሰዎች ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳትን እያስከተለ ነው፡፡

በሙቀት ውስጥ ረጅም ሰዓታትን ማሳለፍ የኤሌክትሮላይት ሚዛን መዛባትን ያስከትላል ይህ ደግሞ ድካም እና ማዞር እንዲሁም ራስን መሳት ያስከትላል ሲሉ ባለሙያዎች ገልፀዋል።

እንደ የልብ ሕመም ወይም የደም ግፊት ያሉ ተጓዳኝ በሽታዎች ያለባቸው ግለሰቦች ከሙቀት ጋር የተያያዙ ችግሮች የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው ሲሉ የህክምና ባለሙያዎች ተናረዋል፡፡ በዚህም መራጮች የሙቀቱ ስጋት ቢያድርባቸውም ቅድመ ጥንቃቄ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

ባለፈው ዓመት 2023 ህንድ ከ1901 ጀምሮ ሁለተኛው ሞቃታማ ዓመት ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን በዛው አመት ወደ 264 የሚጠጉ ሰዎች በሙቀት ሳቢያ መሞታቸው የሀገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

Tags: global warminghigh temperaturetemperature
ShareTweetShare
Previous Post

አጫጭር የስፖርት መረጃዎች

Next Post

አጫጭር የሀገር ውስጥ መረጃዎች

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
አጫጭር የሀገር ውስጥ መረጃዎች

አጫጭር የሀገር ውስጥ መረጃዎች

ዓለምን በአንድ መዳፍ ያደረገው

ዓለምን በአንድ መዳፍ ያደረገው

በኮንትሮባንድ ስራ ላይ የተገኙ 745 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ

በኮንትሮባንድ ስራ ላይ የተገኙ 745 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?