፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 05 2016| NBC ETHIOPIA-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በጎንደር የሚገኙ ሶስት እጅግ አስፈላጊ ፕሮጀክቶችን የሥራ አፈፃፀም በመገምገም በመጪዎቹ ወራት ተፋጥነው እንዲጠናቀቁ የፕሮጀክቶቹ አስተዳደር ማሻሻያ እንዲደረግ መመሪያ ሰጡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በሳምንቱ መጨረሻ በአማራ ክልል ከነበረን ቆይታ ተመልሰን ከከፍተኛ የፌደራል የሥራ ኃላፊዎች ጋር በጎንደር የሚገኙ ሶስት እጅግ አስፈላጊ ፕሮጀክቶችን የሥራ አፈፃፀም በመገምገም የሚጠናቀቁበትን መንገድ አስቀምጠናል ብለዋል።
የፕሮጀክቶቹ ስራዎች የመገጭን ግድብ ማጠናቀቅ፣ የጎንደር ከተማን የውሃ አቅርቦት ማሻሻል እና የአዘዞ ጎንደር 11 ኪሎ ሜትር መንገድ ሥራ መፈፀም ናቸው ሲሉም ገልጸዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












