፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 17 2016| NBC ETHIOPIA-ስርቅታ ደረትን ከሆድ የሚለየው ዋና የመተንፈሻ ጡንቻ (Diaphragm) በድንገት ሲኮማተር ይከሠታል፡፡ ይህ የጡንቻ መኮማተር አየር ወደ ውስጥ እንድናስገባ እና የድምፅ ሳጥን እንዲዘጋ ያደርጋል። በዚህን ጊዜም ”ስርቅ” የሚለው ድምፅ ወይም ስርቅታ ይፈጠራል።

የስርቅታ መንስኤዎቹ ምንድናቸው?
በ 48 ሰዓታት ውስጥ የሚጠፋ ስርቅታን የሚያመጡ መንሥኤዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ።

የስርቅታ መንስኤዎቹ ምንድናቸው?
በ 48 ሰዓታት ውስጥ የሚጠፋ ስርቅታን የሚያመጡ መንሥኤዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ።
-በአንድ ጊዜ ከመጠን በላይ ምግብ መመገብ
-የአልኮል መጠጦች ወይም እንደ ኮካ ያሉ ጋዝ ያላቸው ለስላሳ መጠጦች
-ብዙ አየርን በአፍ በኩል ማስገባት፤ ለምሳሌ ማስቲካ በማኘክ ወይም ከረሜላ በመምጠጥ
-ድንገተኛ ደስታ ወይም ጭንቀት በሚፈጠርበት ጊዜም ሊመጣ ይችላል፡፡
-ድንገተኛ የሰውነት ሙቀት መቀየር
በእነዚህ ምክንያት የሚመጣው ስርቅታ አብዛኛውን ጊዜ የሚቆየው ለጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ነው።
ከ48 ሰዓታት በላይ የሚቆይ ስርቅታን (persistent hiccups) የሚያስከትሉ መንስኤዎች ምንድናቸው?
አንዳንድ ጊዜ ግን ስርቅታ መሠረታዊ የጤና ችግር ምልክት ሊሆን ይችላል። ይህ ስርቅታ ከሴቶች ይልቅ በወንዶች ላይ የበለጠ የሚከሠት ሲሆን፤ ምክንያቶቹ እንደሚከተሉት ተጠቅሰዋል።

-የነርቭ ጉዳት ወይም መቆጣት (Phrenic nerve injury)
የመተንፈሻ ጡንቻ እንዲኮማተር በሚያደርጉ ነርቮች ላይ ጉዳትን የሚያደርስ ማንኛውም ዓይነት ሕመም ስርቅታን ሊያመጣ ይችላል።
-በነርቩ ላይ ቀጥተኛ ጉዳት የሚያደርሱ እና ነርቩ የሚገኝበት አካባቢ ያሉ ሕመሞች
– የአንገት ወይም የሆድ ውስጥ ዕጢ
– የጆሮ ታምቡርን የሚነካ ሕመም
– አንዳንድ የጨጓራ ሕመም (GERD)
– የጉሮሮ ኢንፌክሽን
ማዕከላዊ የነርቭ ሥርዓት ችግሮች (Central nervous system disease)
በማዕከላዊው የነርቭ ስርዓት ውስጥ ዕጢ፣ ኢንፌክሽን ወይም ጉዳት ከደረሰ የሰውነትን መደበኛ የነርቭ ቁጥጥርን ሊያስተጓጉል ይችላል። ስለዚህ የመተንፈሻ ጡንቻ ነርቭ የጡንቻ መኮማተር እና ስርቅታን ሊያመጣ ይችላል።
ለምሳሌ ፡-የጭንቅላት ኢንፌክሽን (Encephalitis)
-ማጅራት ገትር ( meningitis)
ስትሮክ (stroke) :- የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ወይም መርጋት የአንጎል ላይ ጉዳት ማድረስ
-የጭንቅላት ዕጢዎች አንዳንድ ሥር የሰደዱ በሽታዎች ስርቅታን ሊያመጡ ይችላሉ።
– የስኳር በሽታ፣ የኩላሊት በሽታ፣ የሰውነት ንጥረ ነገር መዛባት (Electrolyte imbalance)
መድኃኒቶች (Barbiturates,Anesthetics)
ከቀዶ ጥገና ሕክምና በኋላ ስርቅታ ሊከሠት ይችላል አንዳንድ ሰዎች ለቀዶ ጥገና ማደንዘዣ ከወሰዱ በኋላ ወይም የሆድ ዕቃ አካላትን የሚያካትቱ ቀዶ ጥገናዎችን ከአደረጉ በኋላ ስርቅታ ሊይዛቸው ይችላል።
-ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይ ስርቅታ የሚከተሉትን ችግሮች ሊያመጣ ይችላሉ፡፡
-የአመጋገብ መዛባት
-ለመተኛት መቸገር
-በንግግር ጊዜ መቸገር
-ክብደት መቀነስ እና ድካም ሊያስከትል ይችላል፡፡
-ከቀዶ ጥገና በኋላ ቁስል ቶሎ እንዳይድን ሊያደርግ ይችላል።
*ስርቅታን ለማስታገስ የሚከተሉትን የቤት ውስጥ መፍትሔዎች መጠቀም ይችላሉ።

-በወረቀት ከረጢት መተንፈስ
-በቀዝቃዛ ውሃ መጉመጥመጥ
-ትንፋሽን ለጥቂት ሰከንዶች መያዝ
-ቀዝቃዛ ውሃ ፉት ማለት ናቸው።
-ስኳር መቃም ደረቅ ዳቦ መብላት












