፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 162016| NBC ETHIOPIA- ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች በይፋ የብሄራዊ መታወቂያ ምዝገባ ማስጀመሩን አስታወቋል። በ2025 ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ከሚያስፈልጉ አስቻይ ሲስተሞች ውስጥ አንዱ የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ሲሆን ለአካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ከፍተኛ ሚና እንዳለው የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ገልጸዋል ።
የዲጂታል መታወቂያ በሀገር አቀፍ ደረጃ በ2018 ዓ.ም 90 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች ለማዳረስ የታቀደ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ኢትዮ ቴሌኮም በወር በአማካኝ 1 ሚሊዮን ዜጎችን በመመዝገብ ለ32 ሚሊዮን ዜጎች ተደራሽ በማድረግ የሀገራዊ እቅዱን 36 በመቶ ያከናወናል ሲሉ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ገልጸዋል ።


የዲጂታል መታወቂያ ከዜጎች በሚወሰዱ ውስን የባዮሜትሪክስ እና ዲሞግራፊክ መለያ አማካኝነት የተረጋገጠ መረጃ ለማቅረብ የሚያስችል ሲሆን ለአካታች የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት፤ ለቢዝነስ ትስስር፣ ለኢ-ጋቨርመንት አገልግሎት በዳታ የሚመራ የኢኮኖሚ ሥርዓት ለመገንባት፥ ለቀልጣፋ ማህበራዊ አገልግሎት፣ ለተሻለ የዜጎች ህይወት እንዲሁም የሳይበር ማጭበርበርን በመከላከል አስተማማኝ የዲጂታል ስነ-ምህዳር ለመፍጠር የላቀ ሀገራዊ ፋይዳ አለው ተብሏል ።
በ-ሰላማዊት ወልደገሪማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












