Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

በሃገረ ጀርመን እና በእንግሊዝ የተከሰቱ አስገራሚ እውነታዎች

April 17, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨ 

አዲስ አበባ | ሚያዚያ 09 2016| NBC ETHIOPIA-የበርካታ ሁነቶች ስብጥር ናት ዓለም፡፡ በእያንዳንዱ ማዕዘናት ለሰሚ ተመልካቹ ግርምትን  የሚፈጥሩ ሁነቶች አይጠፉም፡፡ ምናልባትም ከቀያችን አሊያም ራቅ ካሉ ቦታዎች ይህም አለ የሚያስብሉ ጉዳዩች በየዕለቱ ይከሰታሉ የተመረጡትን ወደ እናንተ ልናደረስ ወደድን፡፡

የመጀመሪያ አስገራሚ ጉዳያችን ከወደ ጀርመን የተሰማው ነው፡፡ በጀርመን ግዙፍ የሙዚየም ተቋም የሚሰራው የ51 አመቱ የኤግዚቢሽን ቴክኒሻን በቅፅል ስሙ እራሱን “ፍሪላንስ አርቲስት” እያለ ይጠራል፡፡

እናም ይህ አርቲስት የራሱን የጥበብ ስራ በሙዚየሙ ውስጥ ለእይታ በማስቀመጡ ከስራ ገበታው ሊባረር በቅቷል ይላል የሲኤን ኤን ዘገባ፡፡

ለአጭር ጊዜም ብትሆን ህልሙን እንዳሳካ የሚናገረው ጀርመናዊው የጥበብ ስራዬ በታዋቂው ሙዚየም ውስጥ ተሰቅሎ ማየቴ በሰመመን ውስጥ ያለው እንዲመስለኝ አድርጓኛል ይለናል፡፡

የኋላ የኋላ ግን ደስታውን እንኳን በቅጡ ሳያጣጥም ከሰአታት በኋላ እጣፋንታው ከአሰሪዎቹና ከፖሊስ ጋር ግብ ግብ ውስጥ መግባት ሆኖበታል፡፡ 

የሙዚየም ኤግዚቢሽን ባለሙያው  ከሳላቸው ስዕሎች መሃል  አንዱን በታዋቂው በሙኒክ ጀርመን ፒናኮቴክ ዴር ሞዴሬ ተብሎ በሚጠራው ጋለሪው ግድግዳ ላይ ያኖረዋል፡፡

ስዕሎቹን በግድግዳዎቹ ላይ መመልከት የፈጠረለትን ልዩ ስሜት እያጣጣመ የረዥም ጊዜ ህልሙ በግድግዳዎቹ ላይ መመልከቱ እውነት አልመስልህ እያለው  ባለበት ቅጽበት የሙዚየሙ የደህንነት ሃላፊዎች ያለ ፍቃድ በግድግዳው ላይ የተጨመረውን ስዕል በመመልከታቸው ወዲያውኑ ከግድግዳው ላይ አውርደውታል፡፡

ይህም ድርጊት በእጅጉ ያስቆጣቸው የሙዚየሙ ሃላፊዎች የኤግዚቢሽን ቴክኒሻኑን ወዲያውኑ ከስራው አሰናብተውታል፡፡ በዚህ ድርጊቱ ትኩረትን ከመሳብ አልፎ መነጋገሪያ የሆነው የሙዚየሙ ሰራተኛ ያስቀመጠው ስዕል 23.6 ኢንች በ47.2 ኢንች የሚሆን እርዝማኔ የነበረው ነው፡፡ ሥዕሉ በግድግዳው ላይ ለምን ያህል ጊዜ እንደቆየ ባይታወቅም ግለሰቡ ግን ለረጅም ጊዜ እንዳልቆየ ተናግሯል። አሁን ላይ ግለሰቡ በንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ በሚል በምርመራ ላይ እንደሚገኝ ፖሊስ የገለፀ ሲሆን ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ እስከ ሁለት አመት የሚደርስ እስራት እንደሚቀጣ አስታውቋል፡፡

በነገራችን ላይ ይህ አይነቱ ትዕይንት ለሃገረ ጀርመን የመጀመሪያ ክስተት እንዳልሆነ እወቁት ያለው የሲኤን ኤን ዘገባ ከሳምንታት በፊት በጀርመን ቦን በሚገኘው ቡንደስኩንታልት ውስጥ ተከስቶ የነበረው ሁነት ያስታውሳል

በዛ አንዲት ተማሪ  ከስዕሎቿ አንዱን በኤግዚቢሽን ግድግዳ ላይ አንጠልጥላ እንደነበረም ታውቋል፡፡ አስቂኙ ክስተት ደግሞ ሰራተኞቹ ስዕሉን የተመለከቱት የኤግዚቢሽኑ የቆይታ ጊዜ ተጠናቆ በሚያፈርሱበት ወቅት ተጨማሪ የጥበብ ስራ እንዳለ ሲመለከቱ ነበር፡፡

ሌላይኛው አስገራሚ ጉዳያችን ደግሞ በእንግሊዝ ሃገር አንድ ግለሰብ ወጣ እና ለየት ያሉ የጥበብ ስራዎቹን ልዩ ጥበቃ እንዲኖራቸውና እንዲከለሉ በሚል ምክንያት በተከራየው አፓርታማ ላይ በድብቅ ገንብቶ ማስቀመጡ ነው፡፡

እንደ መረጃችን ጥቆማ መሰረት በአደራና በታማኝነት ለሶስት አስርት አመታት ጎጆውን በቀለሰበት አፓርታማ ላይ በአከራዩቹ ንብረት ግርግዳ እና ቁሳቁሶች ሳይቀር  ቀስ በቀስ በድብቅ ወደ ሚፈልገው የጥበብ ስራ ውጤት የቀየረው ግለሰብ ኋላ ላይ አጀብ አስብሏል፡፡

ሁኔታው የታወቀው ግለሰቡ ከሞተ በኃላ ቢሆንም ወጣ ያለ እና ያልተለመደ የጥበብ ውጤት በመሆኑም አሁን ላይ በብሪታንያ መንግስት ጥበቃ እየተደረገለት ይገኛል፡፡

ሮን ጊቲንስ እ.ኤ.አ 2019 በ79 ዓመታቸው ይህን አለም በሞት ከመሰናበታቸው በፊት ቤተሰቦቹ ከዚህ ቀደም ከ1980ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ይኖርበት የነበረውን አፓርታማ ጎብኝተውት እንደነበር ይነገራል፡፡

በወቅቱ በአፓርታማ ውስጥ ያገኙት ነገር በጣም አስደንግጧቸውም ነበር፡፡  ጊቲንስ ቤቱን ሙሉ በሙሉ ታሪካዊ ትዕይንቶችን የሚያሳዩ ሥዕሎች ስሎበታል፡፡ ከሥዕል ሥራዎቹ መካከል የጥንታዊት ግብፅ እና የጆርጂያ እንግሊዝ ምስሎች፤የተቀረጹ እና የተፈለፈሉ የቅሪተ አካላት ውጤቶች እንዲሁም በግድርዳው ላይ ተፈልፍለው የሚገኙ የአንበሳ ጭንቅላት ፍልፍል እና  ሌሎች ግዙፍ የዱር አራዊት ጭንቅላት አምሳያዎች ይገኙበታል።

የጥበብ ባለሙያው ጊቲንስ በህይወት እያለ ሰዎች ቤቱን እንዲጎበኙ እንብዛም ፈቃደኛ እንዳልነበር ይነገርለታል፡፡

የእህቱ ልጅ ዊልያምስ ከሞቱ በኋላ በቴሌፎን ከCNN ጋር ባደረገቸው ቃለ መጠይቅ ስትናገር በቤቱ ውስጥ መግባት ይቅርና ማለፍ የማይታሰብ ነበር ትላለች፡፡ አጎቷ ወጣ ያለ እንግዳ ነገር የሚስተዋልበት እንደሆነ ተናግራለች፡፡ በአለባበሱም ሳይቀር ከከተማው ነዋሪ ወጣ ያለም ነበር ትላለች፡፡

ወደ መገበያያ ጎራ ካለ የሚሸምታቸው በርከት ያሉ የሲሚንቶ ከረጢቶች ነበሩ ትላለች። በተጨማሪም ቤተሰቦቹ እንኳን እንብዛም እንዳይጎበኙት ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ ይህ ባህሪው ነው ስትል ዊልያምስ በነበራት ቆይታ ተናግራለች፡፡ እያንዳንዱ የአፓርታማው ክፍል በከረጢቶች፣ ሳጥኖች፣ መጽሃፎች፣ የጥበብ እቃዎች እና በእጅ የተፃፉ ማስታወሻዎች የተሞሉ ሆነው ተገኝተዋል፡፡  

ShareTweetShare
Previous Post

የሀረሪ ሙዚቃ ላይ ጥልቅ ጥናት የተደረገበት መፅሀፍ ተመረቀ

Next Post

የሀገር ውስጥ አጫጭር መረጃዎች

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
የሀገር ውስጥ አጫጭር መረጃዎች

የሀገር ውስጥ አጫጭር መረጃዎች

አጫጭር የስፖርት መረጃዎች

አጫጭር የስፖርት መረጃዎች

በአለም አዲስ የተሰሙ አስገራሚ ጉዳዮች

በአለም አዲስ የተሰሙ አስገራሚ ጉዳዮች

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?