፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 26፣ 2016| NBC ETHIOPIA-የሳቅ ንጉስ ነው ይሉታል የልጅነት ጊዜያቸውን ያደመቀላቸው፣ ከህጻን እስከ አዋቂ በመላው አለም አድናቂዎች አሉት የሆሊውዱ ፈርጥ በአስቂኝ ድራማዎቹ ዝናን ያተረፈው ሮዋን ሴባስቲያን አትኪንሰን ወይንም ሚስተር ቢን፡፡

ሮዋን አትኪንሰን እንግሊዛዊ ተዋናይ፣ ኮሜዲያን እና ጸሐፊ ነው፡፡ ነገር ግን ዝናን ያተረፈው ሚስተር ቢን በተሰኘው ተከታታይ አስቂኝ ሲትኮም ላይ ነው።
ሮዋን እ.ኤ.አ ጥር 6 1955 ከአባቱ ኤሪክ አትኪንሰን እና ከእናቱ ኤላ ሜይ የቤቱ አራተኛ ልጅ በመሆን በኒውካስል ታይን፣ እንግሊዝ ተወለደ።
መካክለኛ የኑሮ ሁኔታ ላይ ከሚገኙ የገበሬ ቤተሰብ የተገኘው ሮዋን ከልጅነቱ ጀምሮ ቤተሰቦቹን በስራ በማገዝ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በቾሪስተር እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በሴንት ቢስ ትምህርት ቤት ተከታትሏል።
ቀጥሎም አትኪንሰን በኒውካስል ዩኒቨርሲቲ እና በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በመግባት በኤሌክትሪካል እና በኤሌክትሮኒክ ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል።
ሮዋን በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የማስተርስ ዲግሪ ተማሪ በነበረበት ወቅት የ5 ደቂቃ ቲያትር ቃል ሳያወጣ በድርጊት ብቻ ታዳሚዎችን ያስጨበጨበ ትወናን በማሳየት ነበር ትወናን የጀመረው።

ከዛም ከኦክስፎርድ ዩንቨርሲቲ በቲያትር የመጀመሪያ ድግሪው በኤሊክትሪካል ኢንጂነሪንግ ደግሞ ማስተርሱን ይዞ ተመርቋል።
እ.ኤ.አ. በ1979 “The Atkinson People” የተሰኘ በ ቢቢሲ 3 የሬዲዮ ጣቢያ ላይ የተላለፈ አስቂኝ ተከታታይ የሬድዮ ድራማ ላይ በመሳተፍ ድብቁን እና እምቁን ችሎታውን ለህዝብ ማሳየት ቻለ።
ሬዲዮ ላይ የጀመረው የሮዋን ጉዞ ወደ ቴሌቭዥን በማደግ እ.ኤ.አ በ 1979 በለንደን ዊኬንድ ቴሌቭዥን ላይ የተላለፈው Canned Laughter ወይንም የታፈነ ሳቅ የተሰኘ መጠሪያ ባለው አስቂኝ ተከታታይ ድራማ ላይ ለመሳተፍ በቃ።
እ.ኤ.አ በ1986 ለ4 ዓመታት በተላለፈው ብላክ አደር የተሰኘ አስቂኝ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ችሎታውን ማስመስከር ችሏል። በጊዜውም ቢቢሲ ላይ ከተላለፉ እና ስኬታማ መሆን ከቻሉ ሲትኮሞች አንዱ መሆን ችሎ ነበር። ።
ሚስተር ቢን ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ወደ ጥበብ አፍቃሪያን ለመድረስ በሰአቱ ጊዜ አልፈጀበትም ነበር።ነገር ግን ሚስተር ቢን በህይወቱ የተፈተነበት አንድ ነገር ነበር እሱም ሲያወራ ኮልታፋ መሆኑ ነበር ። ሰዎች ኮልታፋ በመሆኑ እጅጉኑ ይቀልዱበት እና ያሾፉበት ነበር ከዛም አልፎ አትችልም ሲሉም ይተቹት ነበር።
ታዲያ ለዚህ ችግር መፍትሄ በማሰብ ዝምተኛውን ነገር ግን እጅግ አስቂኙን የሚስተር ቢንን ገጸባህሪ መላበስን ያስባል።
እናም “በእድሜ ትልቅ የሆነ ሰው ነገር ግን በተግባር የትንሽ ልጅ ገጽባህሪ “ያለውን የሚስተር ቢን ገጽ ባህሪ ይፈጥራል።
እ.ኤ.አ በ 1990 በአስቂኝ ትዕይንቶች የተሞላውን ሚስተር ቢን የተሰኘውን አስቂኝ ተከታታይ ሲትኮም እራሱ በመተውን ለህዝን ማድረስ ቻለ። የሚስተር ቢን ገጽ ባህሪም በዕለት ተዕለት ተግባራት የሚገጥሙትን የተለያዩ ችግሮችን ለመፍታት ሲሞክር የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቷች የሚያሳይ አስቅኝ ድራማ ነበር።
የገጸ-ባህሪው ራስ ወዳድነት, የልጅነት ስብዕና,እና ከሥነ ምግባር ባህሪው, የፊት ገጽታው እና ከድምጽ አልባ ድርጊቶቹ ጋር ተዳምሮ ተወዳጅ እንዲሆን አስችሎታል።
ሚስተር ቢን ከሬዲዮ እና ከቴሌቭዥን ሲትኮሞች በተጨማሪ ወደ ፊልሞች ላይ በመምጣት ጄምስ ቦንድ ፣ ኔቨር ሴይ ኔቨር አጌን፣ ናይጄል ሃውቶርን፣ ላይ በመሪነት በመሳተፍ ድንቅ ችሎታውን አስመስክሯል።
ሚስተር ቢን እ.ኤ.አ. በ1990 የሞንትሬክስ Festival Golden Rose ሽልማት ፣ በ1991 አለም አቀፍ ኤምሚ ምርጥ ታዋቂ የስነጥበብ ፕሮግራም እና በ1994 የአሜሪካ የኬብል Ace ሽልማት አሸንፈዋል።
“ስኬታማ ለመሆን ቆንጆ ፊት እና የጀግንነት አካል አያስፈልግም፣ የሚያስፈልግህ ችሎታ ያለው አእምሮ እና የመስራት ብቃት ነው”። የሮዋን አትኪንሰን ድንቅ የሆነ ንግግር ነው።
በ-ሀይማኖትወርቁ












