አዲስ አበባ | መጋቢት 26፣ 2016| NBC ETHIOPIA- የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ሥራ ለመጀመር ያስፈልገኛል ብሎ ካቀደው ከሁለት እጥፍ በላይ የሆነ ተሳትፎን በማሳካት ካፒታል የማሰባሰብ ሂደቱን ማጠናቀቁን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

በህዳር ወር 2016 ዓ.ም የተጀመረው ይህ በገበያው የሥራ አመራር አባላትና በአማካሪዎቹ ብርቱ ጥረት በአዲስ አበባ፣ ናይሮቢና ሎንዶን በተደረጉ ባለሀብቶችን የማግባባትና የማሳመን ሥራዎች ከሀገር ውስጥና ከውጪ ባለሀብቶች ከተጠበቀው በላይ የሆነ ምላሽን በማግኘት በድምሩ ብር 1.5 ቢሊዮን (26.6 ሚሊዮን)ዶላር ካፒታል ማሰባሰብ ችሏል።
ገበያው ግንባር ቀደም በሆነ የግልና የመንግስት አጋርነት በጥቅምት 2016 ዓ.ም. የተቋቋመ ሲሆን መንግስት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በኩል የ25% የተፈቀደ ካፒታል ድርሻ ሲይዝ የግል ዘርፉ ደግሞ ቀሪውን 75% ድርሻ ይዟል።
የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያው በመጪዎቹ ወራት ወደ ሥራ ለማስገባት ወሳኝ የሆኑ ተግባራትን እያከናወነ እና ዋና ዋና ስራዎቹን በማጠናቀቅ ላይ መሆኑን ይፋ አድርጓል።
በ ፀጋሁን አሰፋ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












