አዲስ አበባ | ጥር 09፤ 2016| NBC ETHIOPIA – የከተራና የጥምቀት በዓልን ተከትሎ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይኖር ለትራፊክ ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በጥምቀት በዓል በርካታ ህዝብ ታቦታትን አጅቦ ከተለያዩ ቤተ-ክርስቲያናት ወደ ጥምቀተ ባህር የሚንቀሳቀስ በመሆኑ በትራፊክ ፍሰቱ ላይ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ታቦታቱ በሚጓዙባቸው መንገዶች ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓታት አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡
በተለይም በርካታ ህዝብ በሚታደምበት በጃንሜዳ ከጥቅምት 10 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ታቦታት ወደ መንበረ ክብራቸው እስኪመለሱ መንገዶቹ ለተሸከርካሪዎች ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ በዚህም መሰረት ፡-
- ከ6ኪሎ አደባባይ እስከ 3ተኛ ሻለቃ ፈረንሳይ ለጋሲዬን መንገድ
- ከ3ኛ ሻለቃ አደባባይ በምንሊክ ሆስፒታል እስከ ቀበና አደባባይ
- ከምንሊክ ሆስፒታል እስከ 6 ኪሎ ታክሲ ተራ
- ከቅድስተ ማርያም ቤ/ክርስቲያን እስከ 6 ኪሎ፣
- ከ6ኪሎ እስከ መነን፣
- ከሀምሌ 19 እስከ ግብፅ ኢምባሲ፣
- ከቅድስተ ማሪያም መነጽረወ ተራ እስከ ጃንሜዳ፣
- ከግንፍሌ ድልድይ ምንሊክ ሆስፒታል ውስጥ ለውስጥ፣
- ከግንፍሌ መገንጠያ ምንሊክ ሆስፒታል ፊት ለፊት፣
- ከምንሊክ ሆስፒታል የኋላ በር እስከ ቤላ መገንጠያ ድረስ፣ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በዓሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በጃን ሜዳና በዙሪያው ተሽከርካሪ አቆሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ የገለፀሲሆን አሽከርካሪዎች የትራፊክ ፖሊስ አባላትን ትእዛዝ በመቀበል የድርሻቸውን እንዲወጡ የአዲስ አበባ ፖሊስ በማህበራዊ ትስስር ገጽ ባስተላለፈው መልእክቱ አስታውቋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












