አዲስ አበባ | ታህሳስ 10፤ 2016| NBC ETHIOPIA- የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ በገቢ አሰባሰብ፣ በንግድ ስራዎች በተከናወኑ ስራዎች እና በቀጣይ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ሊሰሩ በታቀዱ ስራዎች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ቢኒያም መኩሪያ በመግለጫው የከተማ አስተዳደሩ በ6.3 ቢሊየን ብር ወጪ በማድረግ በአምስቱም የከተማ መግቢያ በሮች ላይ የገበያ ማዕከላት መገንባታቸውን በመግለጫው ገልፀዋል።
የንግዱ ማህበረሰብ የሚያጋጠመውን ችግሮች በቅርበት ለመነጋገር እንዲሁም ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠር በማለም በየደረጃው ከሚገኙ ግብር ከፋዮች ጋር ውይይቶቹ እየተካሄዱ እንደሚገኝ የቢሮዎቹ ሀላፊዎች አስታውቀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ በተገኙበት በቀጣይ ሁሉንም የንግድ ማህበረሰብ ያካተተ ውይይት እንደሚካሄድ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በበጀት አመቱ ለመሰብሰብ ያቀደውን ከ140ቢሊየን ብር በላይ ከግብ ለማድረስ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በስምምነት እየሰራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር አደም ኑሪ አስታውሰዋል።
ቢሮው ከ33 ቢሊየን ብር ወደ 140 ቢሊየን ብር ግብር የመሰብሰብ አቅሙን ያሳደገ ሲሆን ይህም 26 በመቶ እድገት ማሳየቱን የቢሮው ሀላፊ አንስተዋል። በአዲስ አበባ ከተማ ከ470ሺ በላይ ግብር ከፋዮች ይገኛሉ።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












