አዲስ አበባ | ህዳር 20 ፤ 2016| NBC ETHIOPIA – የትምህርት ሚኒስቴር አንዲት ሴት በወሊድ ምክንያት ከ15 ቀን በላይ በትምህርት ገበታዋ ካልተገኘች ትምህርቷን መቀጠል እንደማትችል የሚደነግግ ረቂቅ መመሪያ ማዘጋጀቱ ከሰሞኑ ይፋ ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ የህግ ባለሞያዎች ሴቶች ማህበር ረቂቅ መመሪያው የሴቶችን የመማር ሰብአዊ መብት እንዲሁም የወሊድ ፍቃድ መብትን የሚገድብ ነው ሲል ተቋሙሞታል።
በመመሪያው አንዲት ሴት ከ16 ቀናት እና ከዛ በላይ ከትምህርት ገበታዋ የምትቀር ከሆነ በዚያ አመት የጀመረችውን ትምህርት እንድታቋርጥ፣ ነገር ግን በቀጠይ ዓመት ፍላጎቱ ካላት ተምህርቷን መቀጠል ትችላለች የሚል ረቂቅ መመሪያ ነው ያዘጋጀው፡፡
ሚኒስቴሩ ባዘጋጀው መመሪያ ላይ ሴት ተማሪዎች በወሊድ ምክንያት ትምህርታቸውን እንዳያቋሩጡ አማራጭ መፍትሔዎችን አልያም ማካካሻዎች ያላካተተ በመሆኑ የሴቶችን የመማር መብት እና የሚያደርሰውን ስነ ልቦናዊ ጫና ያላገናዘበ ነው ሲል የኢትዮጵያ የህግ ባለሞያዎች ሴቶች ማህበር ረቂቁን ተችቶታል ።
ማህበሩ ከአጋር ማህበራት ጋር በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ትምህርት ሚኒስቴር መመሪያውን ደግሞ በአፅንኦት ሊመለከተው ይገባል ሲል አሳስቧል።
በሀሴት ሀይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












