አዲስ አበባ | ህዳር 19፤ 2016| NBC ETHIOPIA – የ2016/17 ምርት ዘመን የታቀደውን 19 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥእና ስርጭት ካለፉት ዓመታት የተሻለ እንደሚሆን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፍያ ካሳ(ዶ/ር) የ2016/17 ምርት ዘመን አፈር ማዳበሪያ ግዥ እና ስርጭት ካለፉት ዓመታት የተሻለ እንደሚሆን አንስተዋል።
ለዘንድሮ የአፈር ማዳበራያ ለማሻሻል ከዚህ ቀደም የነበረውን የግዢ መመሪያ መቀየር፣የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን በአዲስ መልክ እንዲደራጅ ማድረግ ፣የተለያዩ የግዢ አማራጮችን በመጠቀም እንዲሁም በወቅት እየተከፋፈለ አስፈላጊ አቅርቦት እንዲደርስ ይደረጋል ብለዋል።
የ2016/17 የምርት ዘመን አፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ከባለፉት ሁለት ዓመታት የተሻለ መደረጉ አርሶአደሩ ከዚህ ቀደም በሚገዛበት ዋጋ እንዲያገኝ ይረደዋል ተብሏል።
የ2016/17 ምርት ዘመን ከታቀደውን 19 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥእና ስርጭት ካለፉት ዓመታት የተሻለ እንደሚሆን ተነስቷል፡፡
በሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












