አዲስ አበባ | ጥቅምት 01 2016| NBC ETHIOPIA -ቤተሰብ የአንድ ማህበረሰብ ብሎም የሀገር መሰረት ነው። ልጆች የየትኛውም ማህበረሰብ የጋራ ስራ ውጤት ናቸው፡፡ አብዛኛውን የልጆች ማሳደግ ሃላፊነት ቤተሰብ ይወስዳል፡፡

የስነ- ልቦና ባለሙያዎች ቤተሰቦች የሚወስዱትን ሃላፊነት እና ከልጆቻቸው ጋር የሚኖራቸውን መስተጋብር እንደሚከተሉት ይከፍሉታል።
1. ገደብ ገዢ (Authoritative) :-

ከልጆች ጋር በመነጋገር የሚያምን እና ችግርን በጋራ የሚፈታ ግልጽ የሆኑ የጋራ ህጎችን እና ግቦችን የሚያስቀምጥ የሁለትዮሽ ንግግር እና ሃሳብ ቦታ የሚሰጥ
ለምሳሌ፡ የልጅን ጥፋት ለምን ብሎ የሚጠይቅ ፡ በምክያት እንዳይደገም የሚመክር ቤተሰብ
2. ገዢ (Authoritarian):

በቤተሰብ ፍላጎት እና ፈቃድ ብቻ በአንድ አቅጣጫ የሚመራ ቀጥተኛ ህገ ደንብ የተቀመጠለት እምብዛም ለልጆች ስሜት እና ባሕሪይ የማይጨነቅ ቅጣትን እንደ ሕግ ማስፈጸሚያ እና ሥርዓት ማስጠበቂያ የሚቆጥር
ለምሳሌ ፡ ዋ ዋ . . . አብዝቶ የሚጠቀም ፡ ቅጣትን በማብዛት ልጆችን ለማረም የሚሞክር
3. የሚያሞላቅቅ (Permissive):

በልጆች ፍላጎት እና ፍቃድ የሚመራ ደንብ የሌለው ከልጆች ጋር ግጭትን የማይወድ ሁሉን የሚፈቅድ ቤተሰብ
ለምሳሌ ፡ ሁሉን በመፍቀድ እና በማድረግ የሚመጻደቅ
4. ቸልተኛ (Neglectful):

በልጆች ሕይወት ውስጥ ስለምንም ግድ የሌለው በልጆች ውሎ ፣ እድገት እና ስኬት ብሎም ማኅበራዊ ፣ ስሜታዊ እና የባህሪይ ፍላጎት ደንታ የማይሰጠው
ለምሳሌ ፡ የልጆች ማጥናት ፣ የቤት ስራ እና የትምህርት ውጤት ትዝ የማይለው
የትኛው የቤተሰብ አይነት የተሻለ ውጤት ያመጣል ? ሀሳብዎን ያጋሩን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












