አዲስ አበባ | መስከረም 29 2016| NBC ETHIOPIA – ኤዲን ሃዛርድ ከእግር ኳስ በጡረታ መገለሉን አስታውቋል።

የቀድሞው የሊል፣ ቼልሲና ሪያል ማድሪድ አጥቂ ገና በ32 አመቱ ነው ጫማውን መስቀሉን ይፋ ያደረገው።
ቤልጂየማዊው የመስመር አጥቂ ፣ ከሪያል ማድሪድ ጋር የነበረውን ዉል ባሳለፍነው ሰኔ ወር በስምምነት ካቋረጠ በኋላ ክለብ አላገኘም ነበር።
በመዲናው ክለብ በነበረው የአራት አመት ቆይታ በ76 ጨዋታዎች ላይ ብቻ ነበር የተሰለፈው።
ዉሉን ማቋረጡ ከተሰማ በኋላ ጥቂት የእንግሊዝ ክለቦች የማዘዋወር ፍላጎት አሳይተው ነበር።
ይሁንና የገባበት የብቃት መውረድ ፈተና ለዝውውሩ እንቅፋት ሆኖ ለክለብ አልባነት ዳርጎታል።
ሃዛርድ ጫማ መስቀሉን በኢንስታግራም ገጹ በኩል ነው እወቁልኝ ያለው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












