
ትዕግስት አሰፋ እና ጉዬ አዶላ የበርሊን ማራቶንን አሸነፉ።
በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ አንደኛ ሆኖ ስታጠናቅቅ የመጨረሻዎቹን ኪሎ ሜትሮች ከጉዳት ጋ እየታገለች ነው።
የዓለም ክብረወሰን የመስበር እቅዷን ባታሳካም ጽናቷን ያሳየችበት ድል ሆኗል።
ትዕግስት የበርሊን ማራቶንን ስታሸንፍ ለሦስተኛ ጊዜ ነው።
የገባችበት 2:11:04 በታሪክ ሶስተኛው ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል።
ኢትዮጵያውያን እስከ 5ኛ በተከታታይ ገብተዋል፤ በዳቱ ሂርጶና ደራ ዲዳ ሁለተኛና ሶስተኛ ወጥተዋል።
በወንዶች አትሌት ጉዬ አዶላ 2፡02፡51 በሆነ ጊዜ በመጨረስ የግል ምርጥ ሰዓቱን በማስመዝገብ የውድድሩ አሸናፊ ሆኗል።

አትሌቱ የበርሊን ማራቶንን ለሁለተኛ ጊዜ አሸንፏል።
ገመቹ ዲዳ በ2፡03፡19 2ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።












