
ናሽናል ሚድያ አክስዮን ማህበር (NBC ETHIOPIA TV) ያዘጋጀው የ“አዲሲቱ አዲስ” የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ነው።
መድረኩ አዲስ አበባ ከትላንት እስከ ዛሬ ያለፈችበት የከተማነት እድገት ጉዞ እንዲሁም በሁሉም መስክ እየተከናወኑ ያሉ ከተማዋን የማደስና የልማት ሥራዎች፣ መልካም እድሎችና ተግዳሮቶች ላይ በስፋት ውይይት እየተካሄደበት ነው።
የከተማነት ጉዞ ከትናንት እስከ ዛሬ እሳቤውና አፈፃፀሙ፣ስኬትና ተግዳሮቶቹ ምን እንደሆኑ በጥልቀት በመጠየቅ የለውጥ አመራርና የሥራ አፈጻጸም እውን ለማድረግ መድረኩ ወሳኝ መሆኑን የኤን ቢ ሲ ኢትዮጵያ ምክትል ስራ አስፈጻሚ ዘካሪያስ ብርሃኑ ገልጸዋል።
አዲስ አበባ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በፈጣን እድገት ላይ ትገኛለች ያሉት ምክትል ስራ አስፈጻሚው ከከተማ ማደስ እና ከተማ መቀየር ጋር ተያይዞ የታየው ለውጥ የሚያስደንቅ መሆኑን አመላክተዋል።
በመድረኩ የአዲስ አባበን ከትናንት እስከ ዛሬ የከተሜነት ሂደት የተመለከ ጥናታዊ ጽሁፍ እየቀረበ ይገኛል።
በ – ሰላማዊት ወልደገሪማ












