Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

በሀገራዊ ምክክር ሂደት ከትግራይ ባለድርሻ አካላት ምን ይጠበቃል?

በሀገራዊ ምክክር ሂደት ከትግራይ ባለድርሻ አካላት ምን ይጠበቃል?

December 29, 2025
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

NBC Ethiopia

December 29, 2025

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገራችን ኢትዮጵያ በፖለቲካ እና ሃሳብ መሪዎች፤ መንግስት እና የሕብረተሰብ ክፍሎች መካከል እጅግ መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ለዘመናት ሲንከባለሉ የቆዩ የሃሳብ ልዩነቶችን እና አለመግባባቶችን በምክክር ለመፍታት የተቋቋመ ነፃና ገለልተኛ ተቋም መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህ መነሻነት ኮሚሽኑ እስካሁን በ11 ክልሎች፣ በ2 የከተማ አስተዳደሮች፣ በፌዴራል ባለድርሻ አካላት፣ በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም በተለያዩ መንገዶች አጀንዳን አሰባስቧል፡፡

በዚህ መሰረት ኮሚሽኑ በሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች እንዳደረገው ሁሉ በትግራይም ክልል የምክክር ሂደቶችን ለማከናወን እንደተዘጋጀ በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲገልፅ ቆይቷል፡፡ ከዚህ ዝግጅት ጋር በተያየዘ ኮሚሽኑ ከትግራይ ባለድርሻ አካላት ጋር ገንቢ የሚባሉ ግንኙነቶችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

በመሆኑም ኮሚሽኑ በክልሉ ውስጥ ለሚያካሂዳቸው የምክክር ሥራዎች የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የሚከተሉትን ተግባራት በኃላፊነት እንዲወጡ እና የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እገዛ እንዲያደርጉ ኮሚሽኑ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

1. ህዝባዊነትን ማስቀደም

በትግራይ ክልል የሚገኙ የፖለቲካ ኃይሎች፣ የሲቪክ ማህበራት ፣የማህበረሰብ መሪዎች፣ መገናኛ ብዙሃን፣ በጎ ተፅዕኖን የሚፈጥሩ ግለሰቦች፣ ወዘተ ሀገራዊ ምክክሩ ከምንም በላይ ኢትዮጵያዊያን በነገ ተስፋቸው ላይ የሚወያዩበት መድረክ መሆኑን መገንዘብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት አካላትም ሆነ ሌሎች ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ሀገራዊ ምክክሩን በተመለከተ እስካሁን ያበረከቱት አስተዋፅኦ የሚደነቅ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ሂደቱን የሚደግፉና መሰል ግንዛቤዎችን ለወገኖቻቸው ማስረፅ ይገባቸዋል፡፡

2. የሂደቱን ባለቤትነት መጋራት

በትግራይ ክልል በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ሕብረተሰቡ በሂደቱ ላይ የጎላ የባለቤትነት መንፈስ እንዲሰማው የማስተማር ብሎም የማስገንዘብ ሥራዎችን ማከናወን ይጠበቅባቸዋል፡፡ በሂደቱ ላይ የትግራይ ህዝብ ድምፁን በተገቢው ሁኔታ አለማሰማቱ የሚኖረው እንድምታ በቀላሉ መታየት ስለሌለበት፤ እንዲሁም እንዲህ ዓይነቱ ክፍተት የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ከቆመለት ዓላማ ጋር ስለሚፃረር በጥልቀት እና በአስተውሎት ሊታሰብበት ይገባል፡፡

3. ሞራልን መሰረት ያደረጉ አቅጣጫዎችን መጠቆም

የሃይማኖት ተቋማት፣ ምሁራን እና የመገናኛ ብዙሃን የማህበረሰብ ሕሊና በመሆን እንደሚያገለግሉ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በዚህ መነሻነት እነዚህ ተቋማት ሕብረተሰቡን ሀገራዊ ምክክር የአንድ ጊዜ ክስተት ሳይሆን የዘላቂ መግባባት እና ሰላም መንገድ እንደሆነ አቅጣጫ በማሳየት በሀገሩ ኢትዮጵያ ላይ ለዘለቄታው የሚበጁ የመፍትሔ ሀሳቦችን ከሌሎች ወገኖቹ ጋር እንዲያመነጭ ማስቻል ይኖርባቸዋል፡፡

Source: @NBCEthiopia
Via: NBC Ethiopia
Tags: EthiopiaFacebookmekeleMeta
ShareTweetShare
Previous Post

ሙዚቀኛው አሰፋ አባተ ማነው?

Next Post

Medemer መተግበሪያ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
Medemer  መተግበሪያ

Medemer መተግበሪያ

የኢትዮጵያ ቡናን በቻይና ገበያ የበለጠ ለማስተዋወቅ እና ኤክስፖርቱን ለማሳደግ ያለመ ኮንፈረንስ በቻይና ሁናን ግዛት እየተካሄደ ነው

የኢትዮጵያ ቡናን በቻይና ገበያ የበለጠ ለማስተዋወቅ እና ኤክስፖርቱን ለማሳደግ ያለመ ኮንፈረንስ በቻይና ሁናን ግዛት እየተካሄደ ነው

የታህሳስ 20 ቀን 2018 ዓ.ም የኤንቢሲ ኢትዮጵያ የምሽት ዜናዎች

የታህሳስ 20 ቀን 2018 ዓ.ም የኤንቢሲ ኢትዮጵያ የምሽት ዜናዎች

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?