የኒው ዮርክ ከንቲባ በመሆን በምርጫ ያሸኘፉት የ34 አመቱ ዞህራን ማምዳኒ ከምርጫ በኋላ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸው የሽግግር ቡድናቸው የአመራር ሂደት አስታውቀዋል።
በዚህም በመጪዎቹ ጊዜያት በሚኖራቸው የኒው ዮርክ ከተማ ከንቲባነት ቆይታ፤ የምርጫ መድረኮችን ወደ ፖሊሲዎች ለመቀየር: ብቁና የህዝቡን ችግሮች የሚያደምጥ አስተዳደር ለመመስረት ቃል ገብተዋል። በሚቀጥሉት ወራት እኔና ቡድኔ በምርጫ ዘመቻ የገባናቸውን ቃሎች እውን የሚያደርግ ማዘጋጃ ቤት እንመሰርታለን ብለዋል።
የዴሞክራቲክ ፖርቲ አባል የሆኑት ዞህራን ማምዲኒ ፤ በዶናልድ ትራምፕ የተመለሱትን ዴሞክራት አንድሪው ኩዋሞ እንዲሁም ሪፐብሊካን እጩዋ ኩርቲስ ስሊዋን በማሸነፍ ነው የኒው ዮርክ ከንቲባ የሆኑት።
የ34 አመቱ ዞህራን ማምዳኒ ከአውሮፓውያኑ 1890ዎቹ ወዲህ የመጀመሪያው ወጣት የኒው ዮርክ ከንቲባ ያደርጋቸዋል ። የመጀመሪያው የኒው ዮርክ ሙስሊም እና የደቡብ እስያ የዘር ሀረግ ያላቸው ከንቲባም ሆነዋል።
ዞህራን ማምዳኒ በመጪው የፈረንጆቹ ጥር 1/2026 ቃለ መሀላ በመፈፀም ስልጣነ መንበሩን ይረከባሉ።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
በ-የአብስራ ሚሊዮን












