የኬያኒያው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራኢላ ዖዲንጋ በ80 ዓመታቸው አረፉ።
በኪንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለአምስት ጊዚያት ያህል የተወዳደሩ ሲሆን ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በአገሪቱ ፖለቲካ ላይ ትልቅ ተሳትፎ ነበራቸው። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ራኢላ ኦዲንጋ በልብ ድካም ህመም ህንድ ውስጥ ማረፋቸውም ተሰምቷል።
በተሳተፉባቸው ምርጫዎች ሁሉ ቅሬታ በማቅረብ አገሪቱን ከሚመሩ መንግስታት ጋር በየደጋጋሚ ውጥረት ውስጥ በመግባትም ይታወቃሉ። አባታቸው በኬንያ ፖለቲካ ውስጥ ቁልፍ ሚና የነበራቸው እንደነበሩም ታሪካቸው ያሳያል።
የኬንያ የመጀመሪያው ምክትል ፕሬዚዳንትም ነበሩ ጃራሞጂ ዖጊንጋ ዖዲንጋ የራኢላ ዖዲንጋ አባት።
ዘገባው የሮይተርስ ነው
በ-ቢኒያም ካሴ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












