በመጪው በጋ ወራት ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑ የኢትዮጵያ ክፍሎች መደበኛ እና ከመደበኛ በታች ዝናብ እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሚትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል ። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ባለፈው የክረምት ወቅት ትንበያ ግምገማ እና የመጪው በጋ ወቅት ትንበያ ይፋ የሚያደርግበት መድረክ እያካሄደ ነው።
ኢንስቲትዩቱ የ2018 የበጋ የዝናብ ሁኔታን አስመልክቶ በሰጠው ማብራሪያም፣ በሀገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች መደበኛ እንዲሁም ከመደበኛ በታች ዝናብ ሊኖር እንደሚችል ነው ትንበያውን ያስቀመጠው። የ2018 የበጋ የዝናብ ወቅት በአብዛኛው አካባቢዎች ላይ መስከረም መጨረሻ ይጀምራል ተብሎ የተተነበየ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎች ግን ጥቅምት ይጀመራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ በታች የዝናብ ስርጭት እንደሚኖራቸው የተገለፀ ሲሆን ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ኢትዮጵያ አከባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚጠበቅም በትንበያው ተቀምጧል።
ይህ የበጋ ወቅት የዝናብ ሁኔታ በግብርና፣ በውሃ ተፋሰስ አካላት እና በጤና ሴክተር አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላል የተባለ ሲሆን፣ አስፈላጊው የጥንቃቄ ስራዎች መስራት እንደሚገባም ተመላክቷል ።
በ- ሰላማዊት ወልደገሪማ












