ቤልጂየም ለፍልስጤም ሀገርነት እውቅና እንደምትሰጥ አስታወቀች።
ቤልጂየም መስከረም መጨረሻ በሚካሂደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለፍልስጤም እውቅና ለመስጠት መወሰኗን የቤልጂየም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማክሲም ፕሬቮት አስታውቀዋል።
የሀገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጭምር የሆኑት ፕሬቮት በኤስስ ማህበራዊ ሚዲያ ባሰፈሩት ጽሁፍ “ፍልስጤም በቤልጂየም በተመድ ስብሰባ ላይ እንደ ሀገር እውቅና ታገኛለች! በእስራኤል መንግስት ላይም ጠንካራ ማዕቀቦች ይጣላሉ” ሲሉ ገልጸዋል ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሀገራቸው ለፍልስጤም እውቅና የምትሰጠው በጋዛ የሚገኙ ሁለም ታጋች ለተለቀቁ በኋላ እና “ሐማስ ፍልስጤምን የማስተዳደር ምንም ሚና ከሌለው” ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል። ይህ ውሳኔ ቤልጂየምን ፍልስጤምን እንደ ሀገር እውቅና ከሰጡ ከ140 በላይ አገራት ተርታ እንድትሰለፍ ያደርጋታል።
እስራኤል ከቤልጂየም 12 ማዕቀቦች እንደሚጠብቃት ፕሬቮት ተናግረው፣ በዌስት ባንክ ከሚገኙ ሕገወጥ የእስራኤል ሰፈራዎች የሚመጡ ምርቶች እንዳይገቡ መከልከል ጨምሮ ከእስራኤል ኩባንያዎች ጋር ያሉ የመንግስት የግዥ ፖሊሲዎችን እንደገና መገምገም የሚሉት እንደሚገኙበት ተናግረዋል።
ፕሬቮት አክለው ቤልጂየም እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው በፍልስጤም በተለይም በጋዛ ውስጥ እየተከሰተ ባለው ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
በ- ሰላማዊት ወልደገሪማ












