የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት የ1ሺህ 500ኛውን የታላቁ ነብይ የልደት በዓልን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነብዩ ሙሐመድ ለሰው ልጆች እዝነትን፣መከባበርን፣አብሮ መኖርን ብሎም መተሳሰብን በተግባር ያስተማሩ መሆናቸውን ገልጿል።
ነቢዩ ሙሐመድ ከዘመናት ጠላትነት በኋላ የአረብ ጎሳዎችን በአንድነት ሰንሰለት ያዋሃዱ ታላቅ መሪ መሆናቸውን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ያስታወሰው ጠቅላይ ምክር ቤቱ በዚህም በበርካታ የዘመናችን የታሪክ አዋቂዎች ብሎም የሳይንስ አጥኚዎች ዘንድ ጭምር ከፍተኛ ተቀባይነትን ማግኘት ችለዋል ነው ያለው።
የእሳቸው የልደት በዓል (መውሊድ) በመጪው ሐሙስ በአንዋር መስጂድ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እንደሚከበር ተገልጿል።
በ – አክረም ኑርያ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












