አሜሪካ ዲፕሎማሲን ስትመርጥ አውሮፓውያን ጦር እየናፈቁ እና እየሰበቁ ነው ሲሉ የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ተናገሩ፡፡ የኬቭ አጋሮች እና የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ጥምረት (ኔቶ) በዩክሬን ያለው ጦርነት እንዲቆም አይልጉም የሚል ወቀሳም ላቭሮቭ አቅርበዋል፡፡
ከአላስካው ውይይት በኋላ የኬቭ አጋሮች የተለያየ መግለጫ በመስጠት ዶናልድ ትራምፕ ለሰላም የሚያደርጉትን ጥረት እያስተጓሉ ነው ሲሉ ከአሜሪካው የቴሌቪዥን ጣቢያ ከNBC ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል፡፡
በቃለ ምልልሳቸው የአውሮፓ ተወካዮች “ዩክሬን እንድትሸነፍ፤ ሩሲያ እንድታሸንፍ አንፈልግም” እያሉ የሰላም ፀር እየሆኑ ነው ሲሉ ላቭሮቭ የኬይቭ አጋሮችን ተችተዋል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካን ብሄራዊ ጥቅም የሚያስከብሩ ስለሆኑ እናከብራቸዋለን፤ የአሜሪካ መሪዎችም ፕሬዝዳንት ፑቲን ለሀገራቸው ተመሳሳይ ፍላጎት እንዳለቸው ይረዳሉ ነው ያሉት ላቭሮቭ፡፡
ትራምፕ እና ፑቲን ምንም ምስጢር አላወሩም። እኛም ሰላም እንፈልጋለን ትራምፕም በዩክሬን ሰላም እንዲመጣ ይፈልጋሉ ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
የአላስካውን ውይይት ተከትሎ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ እና አጋሮቻቸው ከትራምፕ ጋር መገናኘታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ለኬይቭ የጸጥታ ዋስትና መስጠት እና ወታደሮቻቸውን ወደ ዩክሬን ለመላክ ማቀዳቸው፤ ሩሲያ ቀይ መስመር መርገጥ ነው ስትል ማስጠንቀቋ አይዘናጋም፡፡
አር ቲ ኒውስ ዘግቦታል፡፡
ቶማይ መኮንን












