የሰሜን ለንደኑ ቶተንሃም ሆትስፐር የአማካኝ ስፍራ ተጫዋች ጉዳቱ ያጋጠመው ከኒውካስትል ዩናይትድ ጋር በተደረገው የአቋም መለኪያ ጨዋታ መሆኑ ተገልጿል።
እንግሊዛዊው ተጫዋች በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር በተደረገ የይሮፓ ሊግ ፍጻሜ የጅማት መበጠስ ጉዳት ማስተናገዱ እና በቀዶ ጥገና ማገገሙ ይታወሳል። አሁን ላይ የገጠመውም ጉዳት በተመሳሳይ ቦታ ላይ ነው የተባለ ሲሆን፤ ከ7 እስከ 8 ወር ከሜዳ እንደሚያርቀው ተዘግቧል።
የክለቡ ሃኪሞች የቀዶ ህክምና እንደሚያደርጉለት እና አዲሱን የውድድር አመት በሙሉ ከሜዳ ሊያርቀው እንደሚችል ግምታቸውን እየሰጡ ይገኛል። ጄምስ ማዲሰን በተጠናቀቀው የውድድር አመት 45 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 12 ግቦችን በስሙ አስመዝግቧል።
ቶተንሃም ሆትስፐር በቀጣይ እስከ ዝውውር መስኮት ፍጻሜ በማዲሰን የመጫወቻ ስፍራ ተተኪውን ሊያመጣ ይችላል ተብሏል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












