ኢራን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዲሁም ከዓለምአቀፉ የአቶሚክ ሀይል ድርጅት የቴክኒክ ቡድን በቴህራን ጉብኝት እንዲያደርግ ፍቃድ ሰጠች።
የቴክኒክ ቡድኑ በመጪዎቹ ሁለት ወይንም ሶስት ሳምንታት ወደ ቴኽራን በማቅናት ጉብኝት ያደርጋል ተብሏል። ቡድኑ የኢራን የአቶሚክ መሰረተ ልማቶችን እንዲጎበኝ ግን እስካሁን ፍቃድ አላገኘም ተብሏል።
የቴኽራን አመራሮች ከእስራኤልና አሜሪካ ጋር በነበረው የአስራ ሁለቱ ቀናት ጦርነት ዓለምአቀፉ የአቶሚክ ሀይል ድርጅት ኢራንን በመሰለል ለእስራኤል መረጃን ሲያሳልፍ ነበር የሚል ተደጋጋሚ ክስ አቅርበዋል።
በጉብኝቱ ወቅት ከኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር የተባበሩት መንግስታት የአቶሚክ ኤጀንሲ ከቴኽራን ጋር ስለሚኖረው ትብብር ይወያያሉም ተብሎ ይጠበቃል።
ሚድል ኢስት ሞኒተር አስነብቦታል
በ-የአብስራ ሚሊዮን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












