የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራንፕ ሀገራቸው ዩኔስኮን ለቃ እንድትወጣ መወሰናቸው ተናግረዋል።
የነጩ ቤተመንግስት ምክትል ቃል አቀባይ አና ከሊ ማክሰኞ ዕለት ለኒዮርክ ፖስት እንደተናገሩት፣ ዩኔስኮ ከፋፋይ ባህላዊና ማኅበራዊ ጉዳዮችን ይደግፋል በማለት አሜሪካ ድርጅቱን ለቃ ትወጣለች ብለዋል። ዩኔስኮና ነጩ ቤተመንግሥት የአሜሪካን መልቀቅ በቶሎ አለመቀበላቸው ተነግሯል።
አሜሪካ ዩኔስኮን ስትለቅ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን፣ የዶናልድ ትራፕ አስተዳደር ከዚህ ቀደም ሀገሪቱን ከዓለም ጤና ድርጅት አባልነትና ከፓሪሱ የአየር ንብረት ስምምነት ማስወጣታቸው ይታወሳል።
ፕሬዝደንቱ ከመጀመሪያ ስልጣን ዘመናቸው አንስተው አሜሪካ ከድርጅቱ እንድትለቅ ሲገፉ የነበር ሲሆን፣ በቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ዳግም ወደ ድርጅቱ መመለስ ችላለች። ይሄው የሀገሪቱ ውሳኔ ከታህሳስ 2026 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተመላክቷል።
”ውሳኔው የሚያሳዝን ነው” በማለት የገለጹት የዬኔስኮ ዋና ዳይሬክተር ኦድሬ አዙሌይ፤ ነገር ግን የሚያስገርም እንዳልሆነና በትራንፕ አስተዳደር ወቅት አሜሪካ ከድርጅቱ መልቀቋ የሚታወቅ ነበር ሲሉ አስታውሰዋል።
ዶናልድ ትራንፕ በ2023 ዳግም ወደስልጣን ከመጡ በኋላ አሜሪካን ከዩኔስኮ የማስወጣቱን ጉዳይ እንደሚገፉበት ይጠበቅ ነበር ብለዋል። የትራንፕ አስተዳደር በ2017 እንዳስታወቀው ዩኔስኮ በእስራኤል ላይ የሚያደርገውን አድልዎ በመጥቀስ ከድርጅቱ እንደምትለቅ ገልጸዋል።
እስራኤልና አሜሪካ ዩኔስኮ ፍልስጤምን አባል ካደረገ በኋላ ለድርጅቱ የሚያደርጉትን የፋይናንስ ድጋፍ በ2011 መቆማቸው ይታወሳል። አሜሪካ ከዚህ ቀደመ በ1984 በሬገን አስተዳደር ዩኔስኮ በወቅቱ ለሶቬት አድሎና ሙስና በተመሎ መንገድ ፍላጎቷን ያራምዳል በማለት ድርጅቱነን የለቀቀች ሲሆን፣ በ2003 በጆርጅ ደብሊው ቡሽ ዘመን ዳግም መመለስ ችላለች።
በ አማኑኤል ምትኩ












