በአሜሪካ “ኪንታኪ” ግዛት በአንድ ቤተ-ክርስቲያን ላይ በተፈጸመ ጥቃት የሁለት ሴቶች ህይወት የቀጠፈ።
በፖሊስ ኦፊሰር ላይ መተኮስ የጀመረው ታጣቂው የሁለት ሰዎችን ህይወት ከመቅጠፉም ባሻገር በፖሊስ ባልደረባ ላይ ጉዳት አድርሷል። ጥቃት ፈጻሚው ወደ ሪችመንድ ሮድ ባፕቲስት ቸርች በማሽከርከር ጥሶ ገብቶ በምዕመናኑ ላይ ተኩስ ከፍቷል፡፡
የህግ አስከባሪ ሀይሎች ተኩሰው የገደሉት ሲሆን፣ አሜሪካ ተደጋጋሚ እንዲህ ዓይነት ጥቃቶች እየደረሱባት ይገኛል ተብሏል፡፡ የ72 እና 32 ዓመት ሴቶች መገደላቸው ሲረጋገጥ ሁለት ወንድ ምዕመናን ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
ፖሊስ ተጠርጣሪው በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ካሉ ግለሰቦች ጋር የግል ግንኙነት ሳይኖረው አይቀርም ብሏል፡፡ አሁንም ምርመራው መቀጠሉን የኪንታኪ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ የኪንታኪ ገዥ በኤክስ ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት “በኪንታኪ ምድር እንዲህ ዓይነት ጉዳይ ቦታ የለውም፡፡” ብለዋል።
ቢቢሲ እንዳስነበበው
በ-ቢኒያም ካሴ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












