የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከብራዚል የሚገቡ ምርቶች ላይ የ50 በመቶ የታሪፍ ጭማሪ ዕቅድ ይፉ አደረጉ።
በማህበራዊ ትስስራቸው ባጋሩት ደብዳቤ ከብራዚል ወደ አሜሪካ የሚገቡ ምርቶች ላይ የታሪፍ ጭማሪ ዕቅድ ይፉ ያደረጉ ሲሆን ይህም ከደቡብ አሜሪካ ሀገራት ያለውን መካረር እንዳይጨምረው ተሰግቷል። ትራምፕ አክለውም የቀድሞ የብራዚል ፕሬዝዳንት ቦልሴናሮ ክስ እንዲያበቃ ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀዋል።
የአሜሪካን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ላይ ጥቃት ለማድረስ ሞክራለች የቀድሞውን የብራዚልን ፕሬዝዳንት ቦል ሴናሮ ላይ ግፍ ፈፅማለች ሲሉ ብራዚልን ከሰዋል። የቀድሞ የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ቦልሴናሮ በአውሮፓውያኑ 2022 በተደረገ የብራዚል ምርጫ ለመቀልበስ ተንቀሳቅሰዋል በሚል የክስ ሂደት እየተከታተሉ እንደሆነ ይታወሳል።
ታዲያ የዶናልድ ትራምፕ የታሪፍ ማስፈራሪያና የክስ ሂደት ይቋጭ መልዕክት ተከትሎ የአሁኑ የብራዚል ፕሬዚዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ለታሪፉም ምላሽ እንደሚሰጡ ነገርግን ከሀገራቸው ፍትህ ስርአት ትራምፕ እጃቸውን እንዲሰበስቡ አሳስበዋል።
ሉላ “ብራዚል በፍትህ ስርአት ውስጥ የማንንም ሰው ጣልቃ ገብነት አትቀበልም! ማንንም ከህግ በላይ አይደለም” ብለዋል። ዶናልድ ትራምፕ በማህበራዊ ሚዲያ ባጋሩት መልዕክት ወደ አሜሪካ የሚገቡ የኮፐር ምርቶች ላይ የተጣለው የ50 በመቶ ጭማሪ ከመጪው ነሀሴ 1 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልፀዋል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው።
በ-የአብስራ ሚሊዮን












