
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ከፈረንሳይ፣ ጀርመን እና እንግሊዝ አቻዎቻቸው ጋር ለመነጋገር ወደ ጄኔቫ ለመብረር በተዘጋጁበት ወቅት ነው፤ በመጀመሪያ የእስራኤል ጥቃት መቆም እንደሚገባው ለኢራን የመንግስት ቴሌቪዥን የገለፁት።
አራግቺ፤ በኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ላይ ያለውን ግጭት ለማርገብ ከሶስቱ ሀገራት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ለመገናኘት ስዊዘርላንድ ገብተዋል።
ነገር ግን አራግቺ ለኢራን መንግስት ቴሌቪዥን በሰጡት አስተያየት፣ እስራኤል በአገራቸው ላይ የምታደርገውን ጥቃት እስካላቆመች ለመነጋገር ዝግጁ እንዳልሆኑ ተናግረዋል። አክለውም በእስራኤል ላይ እያደረግነው ካለው ጥቃት በኋላ ሀገሮች ከዚህ ጉዳይ ራሳቸውን የሚያርቁ ይመስለኛል ብለዋል።
በጄኔቫ በሚደረገው ድርድር ላይ የሚሳተፉት የእንግሊዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴቪድ ላሚ፣ ሃሙስ ዕለት ከዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በዋሽንግተን ከተገናኙ በኋላ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ለማምጣት እንሰራለን ብለዋል።
የታቀደው ስብሰባ እስራኤል ባለፈው ሳምንት በኢራን ላይ ጥቃት ከሰነዘረች በኋላ የመጀመሪያው ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
ሔርሜላ ተመስገን












