፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የእስላማዊት ኢራን አብዮታዊ ዘብ (IRGC) አየር ኃይል አዛዥ በእስራኤል ጥቃት ተገደሉ፡፡
አዛዡ መገደላቸውን የእስራኤል መከላከያ ኃይል (IDF) እና የኢራን መገናኛ ብዙኃን አረጋግጠዋል ፡፡
ብርጋዴር ጀነራል አሚር አሊ ሃጂዛዴህ በኢራኑ ሁለንተናዊ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ በ2009 ነበር የአየር ኃይሉ አዛዥ ተደርገው የተሾሙት፡፡
በዋና ከተማዋ ቴህራን በ1953 ዓ.ም የተወለዱት የአየር ኃይሉ አዛዥ የእስራኤል ጥቃት ሰላባ ሆነዋል ፡፡ አብዮታዊ ዘቡን የተቀላቀሉትም በ1980 የነበረ ሲሆን ከ1980–1988 በነበረው የኢራን እና ኢራቅ ጦርነት በተለያዩ ዘመቻዎች ላይም ተሳትፈዋል ይባልላቸዋል ፡፡
በአብዮታዊ ዘቡ የሚሳዔል መርሃ ግብር ውስጥም ሰርተዋል፡፡ ሃጂዛዴህ በአሜሪካ ግምጃ ቤት ማዕቀብ ተጥሎባቸው እንደነበርም ታሪካቸው ያሳያል፡፡
አዛዡ በተለያዩ ዘመቻዎች ላይ ከመሳተፋቸውም ባሻገር የአሜሪካን የአየር ኃይል ጫና ውስጥ በማስገባት ትልቅ ሚና ነበራቸው ተብሏል ፡፡ ለዚህም ነበር ዋሽንግተን ማዕብ የጣለችባቸው፡፡
እስራኤል አዳሩን መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ የኢራን ቁልፍ የጦር አዛዦች ህይዎታቸውን አተዋል፤ከፍተኛ ውድመትም ተከስቷል፡፡
ዘገባው የአልጀዚራ እና ታይምስ ኦፍ እስራኤል ነው፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ












