:::::::::::::::::::::::::::::::::::::
የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ከሩሲያ ባለስልጣናት ጋር ለመደራደር ነዉ ወደ አንካራ ያቀኑት።
ዘለንስኪ አንካራ እንደደረሱ በአውሮፕላን ማረፊያው በሰጡት መግለጫ፤ “እኔ ለድርድር ተገኝቻለሁ ሩሲያ በምን ዓይነት ደረጃ እንደምትገኝ የምናየዉ ይሆናል” ሲሉ ተናግረዋል።
የዩክሬን ልዑክ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት፣ ከጦር ኃይሉ እና ከሁሉም የደህነነት ዘርፎች የተውጣጡ ተወካዮችን ያካተተ እና ከፍተኛ ደረጃ ያለው ነውም ብለዋል ዘለንስኪ።
ሩሲያ ለድርድሩ የምትልከውን የልዑካን ቡድኑ ስብጥር ይፋ ማድረጓ የሚታወስ ነዉ።
ዘለንስኪ ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በአካል ለመገናኘት ፈቃደኛ መሆናቸውን ቢገልጹም፣ ክሬምሊን ግን ፑቲን ለድርድሩ ወደ ቱርክ እንደማይጓዙ አሳውቋል።
ዘገባዉ የቢቢሲ ነዉ
በ- ሊያ ክብሮም












